ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ምስጋን ዝናቤ ከእስር ተፈቱ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 5/2013 ዓ.ም ባህርዳር ///… የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ…

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ምስጋን ዝናቤ ከእስር ተፈቱ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 5/2013 ዓ.ም ባህርዳር ///… የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ እና የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ምስጋን ዝናቤ ዛሬ ሐሙስ ጠዋት ከእስር ተፈትተዋል። ሁለቱ ጋዜጠኞች “ስንጠራችሁ ትመጣላችሁ” በሚል በራሳቸው ዋስ መፈታታቸውን ጋዜጠኛ ተመስገኝ ተናግሯል። ሁለቱ ጋዜጠኞች ትናንት ዘጠኝ ሰዓት ገደማ የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ ሶስት ፖሊሶች እና ሌሎች ሲቪል ለባሽ ግለሰቦች ወደ እስር ቤት መወሰዳቸው ይታወሳል። በወቅቱ ፖሊሶቹም ሆነ ግለሰቦቹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመያዛቸው መዘገቡ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply