ግሎባል አሊያንስ በባህር ዳር ላሉ ተፈናቃዮች የገንዘብ እርዳት አደረገ

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/44157

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

በውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሙት ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (ግሎባል አሊያንስ) ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው ባህርዳር ለሚገኙት የአማራ ክልል ተወላጆች 801 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ተሰማ።

ጥቅምት 16 ቀን 2010 አ/ም ከቤንሻንጉን ጉምዝ የተፈናቀሉት የዓማራ ተወላጆች አሁንም በባህር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን የክልሉም ይሁን የፌዴራል መንግስት ምንም አይነት እርዳታ እንዳላደረገላቸው ይታወቃል።

ተፈናቃዮቹ ችግራችን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መሰማትን ተከትሎ የከተማው ህዝብ እና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከጎናችን አልተለዩም ሲሉ ተደምጠዋል።

ግሎባል አልያንስ የአሁኑን ጨምሮ በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልል በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች የ25 ሺ ዶላር ሲረዳ፤ በወልድያ መንግስት በፈጸመው ጭፍጨፋ ለተገደሉና ለቆሰሉ 21 ቤተሰቦች ለያንዳንዳቸው የ10 ሺ ብር እና በቅርቡ ከእስር ተፈተው ወደ ክልላቸው ለመሄድ ችግር ላጋጠማቸው 33 ከእስት ተፈቺዎች ለያንዳንዳቸው የ10 ሺ ብር እርዳታ ማድረጉ ይታውቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከበሎ ዴዴሣ ቀበሌ መስተዳደር የወጣ የማዘዣ ደብዳቤ እንደሚያሳየው የአማራ ተወላጆች ለሆናችሁ በሙሉ እስከ መጋቢት 30/7/2010 ዓ.ም ድረስ ወይም እስከ ሚያዝያ 10/8/2010 ዓ.ም ሀብታችሁን ሆነ ንብረታችሁን ሽጣችሁ፣ አርዳችሁ የማትወጡ ከሆነ በሕግ ተገዳችሁ እየታሰራችሁ ወዳችሁ ሳይሆን በግድ ትባረራላቹ በማለት መንግስት ተጭማሪ የአማራ ተወላጆችን ከኖሩበት ቦታ ሊያፈነቅል እና በማይወጡት ላይ ለሚደርሰው ችግር ተጠያቂ አለመሆኑን አስታውቋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.