‹‹ ግምገማው ለውጡ በተጀመረው ፍጥነት ወደ ተፈለገው አቅጣጫ እንዲጓዝ ትልቅ እገዛ ያደርጋል›› – ታዬ ደንደአ በኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

አዲስ አበባ:- የኦሮሚያ የብልጽግና ፓርቲ ሰሞኑን ያካሄደው ግምገማ ለውጡ በተጀመረው ፍጥነት ወደ ተፈለገው አቅጣጫ እንዲጓዝ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ የኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ግምገማው ለውጡ በተጀመረው ፍጥነት ወደ ተፈለገው አቅጣጫ እንዲጓዝ ትልቅ እገዛ ያደርጋል።በክልል ደረጃ ከለውጥ ሂደት ጋር ተያይዞ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመገምገም በቀጣይ መወሰድ ስለሚገባቸው ዕርምጃዎች ያመላከተ ነው። በውስጥ ሆኖ ከብልጽግና ዓላማ በተቃራኒ እጁን ሌብነት ውስጥ በመክተት የብልጽግናን ስም የሚያበላሽ፣ የብልጽግናን ካባ ደርቦ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ለህብረተሰቡ ተጨባጭ ውጤት የማያስገኝ መገምገሙን አስታውቀዋል። ብቃት የሌለውን፣ ሌብነት ውስጥ የተሰማራውን፣ በአመለካከትም ችግር ያለበትንም ከብልጽግና መስመር በማግለል

Source: Link to the Post

Leave a Reply