“ግራችንንም፥ ቀኛችንንም ሰጥተን ስለጨረሰን ለብኅውትና የሚሆን ትርፍ ገላ የለንም!” ሲሉ የአብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ገለፁ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      መስ…

“ግራችንንም፥ ቀኛችንንም ሰጥተን ስለጨረሰን ለብኅውትና የሚሆን ትርፍ ገላ የለንም!” ሲሉ የአብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስ…

“ግራችንንም፥ ቀኛችንንም ሰጥተን ስለጨረሰን ለብኅውትና የሚሆን ትርፍ ገላ የለንም!” ሲሉ የአብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው “አማራ ሆይ «ግራህን ሲመቱህ፥ ቀኝህን ጨምርላቸው» የሚለውን ለመኖር እንኳ አልታደልህም፤ እኛ እኮ ለብኅውትና እንኳን የሚሆን ትርፍ ገላ የለንም፤ ሁሉንም ሰጥተን ጨርሰናል። ይልቅ ልንገርህ፦ መሞትህ ካልቀረ አሟሟትህን አሳምር!” የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አቶ ክርስቲያን ሲቀጥሉ መንግስት ጠንካራ ሕዝባዊ ጥያቄዎች በተነሱበት ቁጥር በተለያዩ የአስተዳደር ክልሎች ላይ በሚገኙ አማሮች ላይ ማፈናቀል፣ እስር፣ አፈናና ጅምላ ጭፍጨፋዎች እንደሚፈጠሩ መታዘባቸውን ገልፀዋል። በአማሮች ላይ የሚፈጠሩ ሁሉንአቀፍ ጥፋቶች ተከትሎ ከአማራ ተወላጆች በስተቀር ከአቶ ኦባንግ ሜቶ ውጭ አንድም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ወይም የኢትዮጵያ አንድነት ይገደኛል የሚል አካል ሲያወግዝና ከተጠቂዎች ጎን ሲቆም አይስተዋልም ሲሉ ወቅሰዋል። በተመሳሳይ የኃይማኖት አባቶችም በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው ኅልቆ መሳፍርት የለሽ ሰቆቃና በደል አንድም ቀን አሳስቧቸው ሲያወግዙትና ከእውነት ጎን ሲቆሙ እየተስተዋለ አይደለም ሲሉም አክለዋል። በአማራ ስም ሥልጣን የያዙ አካላት በስሙ ወንበር የተቀመጡበት ሕዝብ ሲሳደድ፣ ሲታፈንና የዘር ማጥፋት ሲፈፀምበት ሕዝባቸውን አስተባብረውና ሥልጣናቸውንም ተጠቅመው ወንጀለኞችን ከመቅጣትና ዘላቂ መፍትሔ ከማበጀት ይልቅ በወገኖቻችን እየደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ ለምን ተናገራችሁ በሚል እኛንኑ ሲያሳድዱ ይውላሉም ብለዋል። የመከላከያ ኤታማዦር ሹሙም ሆኑ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ በመተከል እየተፈፀመ ያለውን የዘር ፍጅት የማስቆም ኦፕሬሽኖችን በመምራት ፋንታ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባዘጋጀው ድግስ መታደምን ስለመምረጣቸው ነው አቶ ክርስቲያን የገለፁት። በአማራ ስም በተፈጠሩ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች የተሰገሰጉ አማራነትን ለግል ፍላጎትና ጥቅማቸው መፈናጠሪያ መሣሪያዊ ማንነት ያደረጉ ተምቾች መተከል ላይ በአማሮች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ፍጅት ትኩረት እንዳያገኝና የወገናቸው ጥቃት ያሳሰባቸው ሁሉ ሙሉ ትኩረታቸውን በዚሁ ላይ እንዳያደርጉ መናኛ አጀንዳዎችን እየወረወሩ ከጨፍጫፊዎች እኩል በሕዝባችን ላይ ስርየት የለሽ ነውር መፈፀማቸውን ቀጥለዋል ሲሉም አክለዋል። አቶ ክርስቲያን “የፍትኅ በትራችን ከሌላው ይልቅ በእናንተ እንደሚበረታና የእጃችሁን እንደምታገኙ ቅንጣት እንኳን አልጠራጠርም!”ሲሉም በገጻቸው አስፍረዋል። የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግስት እንዳንሞት ከመከላከል ይልቅ የገደላችሁ እገሌ ነው በማለት ተጠምዷል ያሉት አቶ ክርስቲያን ገዳዮችን አደብ የማስገዛት ግዴታ ያለበት መንግስት መሆኑን ጠቅሰው ሕወኃት በአሸባሪነት ተፈርጆ ከፓርቲነት በሕግ ይታገድ፤ ኃብቱም ይወረስ ስንል በዝምታ ይሁንታውን የሰጠው ራሱ መንግስት አይደለም ወይ? ሲሉም ጠይቀዋል። በመጨረሻም አማራ ሆይ «ግራህን ሲመቱህ፥ ቀኝህን ጨምርላቸው» የሚለውን ለመኖር እንኳ አልታደልህም፤ እኛ እኮ ለብኅውትና እንኳን የሚሆን ትርፍ ገላ የለንም፤ ሁሉንም ሰጥተን ጨርሰናል። ይልቅ ልንገርህ፦ መሞትህ ካልቀረ አሟሟትህን አሳምር!” የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። እውቁ የታሪክ ተመራማሪ አቶ አቻምየለህ ታምሩ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የጎጃም የነበረው መተከል አማራ የሚታረድበት ቄራ የሆነው ራሱ ብአዴን በፕሮግራም ደረጃ ባደረገው ትግል መሆኑን ጠቅሰዋል። አቶ አቻምየለህ ሲቀጥሉ መተከል ከጎጃም ተወስዶ እንዲህ አማራ የሚታረድበት ቄራ የሆነው አማራው ከሌሎች ነገዶች ጋር ተሰባጥሮ የሚኖርባቸውን አካባቢዎች ሁሉ ብአዴን በ1986 ዓ.ም. ባሳተመው ድርጅታዊ ፕሮግራሙ ላይ «ነፍጠኛውና ትምክህተኛው አማራ ሌሎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችን ለመጨቆን በወራሪነት የሰፈረባቸው የሌሎች ብሔር፣ ብሔረሰቦች ክልሎች ከነፍጠኞች ነጻ ለማድረግ እንታገላለን» ባለው መሰረት እየተፈፀመ ያለ መሆኑን ገልፀዋል። በመሆኑም መተከል የአማራ መታረጃ ቄራ ከመሆን የሚድነውና መላ አማራም ነጻ ሊወጣ የሚችለው የጀመረውን ትግል በብአዴን ላይ ሲያደርግ መሆኑን ነው በመልዕክታቸው ያሰፈሩት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply