ግብጻውያን በህገ መንግስቱ ማሻሻያ ላይ ድምጽ እየሰጡ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/04/%E1%8C%8D%E1%89%A5%E1%8C%BB%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%85%E1%8C%88-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B1-%E1%88%9B%E1%88%BB%E1%88%BB%E1%8B%AB-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8B%B5/

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 12 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብጻውያን የፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አል ሲ ሲን የስልጣን ዘመን ለማራዘም በቀረበው ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ ላይ ህዝበ ውሳኔ እያካሄዱ ነው።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው ህዝበ ውሳኔ የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ዘመን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ለማራዘም በቀረበው ህግ መንግስታዊ ማሻሻያ ላይ ድምጽ ይሰጥበታል።

ማሻሻያው ከጸደቀ የፕሬዚዳንቱን የአንድ ዙር የስልጣን ዘመን ከአራት ወደ ስድስት አመት ያራዝመዋል።

ከዚህ ባለፈም ፕሬዚዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ በምርጫ እንዲወዳደሩም የሚፈቅድላቸው ይሆናል ነው የተባለው።

በፈረንጆቹ 2014 ወደ ስልጣን የመጡት አብዱል ፈታ አል ሲ ሲ በ2022 የስልጣን ዘመናቸው ያበቃል።

የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ዘመን ለማራዘም የቀረበው ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ በሃገሪቱ ፓርላማ በአብላጫ ድምጽ መጽደቁ ይታወሳል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

 

Share this post

One thought on “ግብጻውያን በህገ መንግስቱ ማሻሻያ ላይ ድምጽ እየሰጡ ነው

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.