ግንቦት ሰባት በናዝሬት ላደረገው ባርኔጣዬን አንስቻለሁ #ግርማ_ካሳ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/59596


ግንቦት ሰባት በናዝሬት በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ባሉበት አስደማሚ ሕዝባዊ ትእይንት አድርጓል።
ናዝሬት ሕብረብሄራዊ ከተማ ናት። ዜጎች ኦሮሞ፣አማራ፣ ጉራጌ ሳይባባሉ በሰላም የኖሩባት የተዋለዱባት የፍቅር ምልክት የሆነች ከተማ ናት። ብዙዎቹ ነዋሪዎች ከኦሮሞና ከአማራ፣ ከኦሮሞና ከጉራጐ፣ ከጉራጌና ከአማራ ፣ ከከንባታና ከጉራጌ፣ ከትግሬና ከኦሮሞ ….እያሉ የተዋለዱ ናቸው።
ታዲያ ሕብረብሄራዊ ከተማ በሆነችዋ ናዝሬት አብዛኛው ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ቢሆንም ፣ ኦሮሞዎች ባለቤት በተደረጉበት፣ የኦሮሞ ብቻ በሆነች ክልል ውስጥ ተካታ ፣ የከተማዋና በከተማዋ ያሉ ቀበሌዎች አስተዳደሮች የሚጠቀሙት የስራ ቋንቋ ኦሮምኛ ብቻ ሆኖ፣ አፓርታይዳዊና ዘረኛ አሰራር ነው አጁንም ድረስ ያለው። በናዝሬት ያሉ ከሰባ፣ ሰማኒያ በመቶ በላይ የሚሆኑ ኦሮሞ ያልሆኑ ወገኖች በአገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ነው የሚቆጠሩት።
በአሁኑ

Share this post

One thought on “ግንቦት ሰባት በናዝሬት ላደረገው ባርኔጣዬን አንስቻለሁ #ግርማ_ካሳ

 1. እነ ሌንጮ ለታ አዲስ አበባ ሊገቡ ነው።እንደ ግንቦት ሰባት ያሉም የትጥቅ ትግል የሚሉትን ትተው ወደ ሰላማዊ ትግል እንዱመጡ ጥሪ አቅርቧል
  May 13, 2018
  756
  SHARES
  Share
  Tweet
  ግርማ ካሳ

  የነሌንጫ እርምጃ የሚደገፍ ነው።ሆኖም ብዙ የተለየ አማራጭ ለህዝቡ ያቀርባሉ ብዬ አላስብም። አንደኛ እነዚህ ሰዎች ከኣሮሞ ማህበረሰብ ውጭ ድጋፍ ሊያገኙ አይችልም።ሁለተኛ የነ አቶ ለማ መገርሳና የነ ደር መራራ ድርጅቶች አሉ፣ በህዝብ ተቀባይነት ያላቸው።እና የነርሱ አገር ቤት መግባት ብዙም ዋው የሚያሰኝና አገር ቤት ያለውን ሁኔታ የሚቀይር አይደለም። እነርሱ ከሚገቡ ጃዋር ብቻዉን ቢገባ የበለጠ ንቅናቄ ነው በተለይም ሃረርጌና አርሲ ለፈጥር የሚችለው።

  ግንቦት ሰባት ስም ያለው ግን የተንካታካተ ድርጅት ነው። ሆኖም መሪዎቸ የለ ሌንጮን መንገድ ከተከተሉ በቀላሉ ከተንካታካቱበት ሊያንሰራሩ ይችላሉ። ትልቅ እድል ሊከፈትላቸውም ይችላል። እንደ ግንቦት ሰባት የሰሩት ኪሳራ ቢሆንም በሰላማዊው መንገድ ግን ያኔ በቅንጅት ጊዜ እንዳደረጉት ውጤት ያለው ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።

  ትልቁ ጥያቄ ግን ሻእቢያ ይፈቅድላቸዋል ወይ የሚለው ነው።

  Reply

Leave a Reply to Asmare Cancel reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.