ግንቦት 7 እና ትህዴን እንዲሁም ብአዴን ለአማራ ህዝብ እኩል ናቸው። በሁሉም አይን አማራው “ወንጀለኛ” ነው

Source: http://welkait.com/?p=12011
Print Friendly, PDF & Email

(አያሌ መንበር)

#የሁለቱን (የግንቦት 7 እና ትህዴን(ደህሚት)ን መግልጫ ተመልከቱ

1. “ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተነሱ የፀረ ወያኔ እንቅስቃሴዎች #የበቀል እርምጃ እየተወሰደባቸው ካሉ የህወሃት ካድሬዎች በተጨማሪ #ከህወሃት_ጋር_ምንም_አይነት_ግንኙነት_ያልነበራቸው ሰዎችም #የጥቃቱ ሰልባ እንደሆኑ መስማት እየተለመደ መጥቷል”

#የብአዴን መግለጫንም እዩት፦

2. “አንዳንዶቹ የግጭት አዝማሚያዎች “#ማንነትን” እየለዩ ጥቃት የሚሰነዘርባቸው ናቸው።

የሁለቱ መግለጫ ሲደመር በትህነግ አጋዚ እና መከላከያ ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸው አማራዎች

1. መገዳለቸው ትክክል ነው።
2. አማራውን የደረሰበት የዘር ጥቃት የለም።
3. አማራው አፀፋ መመለሱ ስህተት ነው።
3. አማራዎች በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎ ራሳቸውን ሲከላከሉና በአፀፋ ሲመልሱ ከስርዓቱ ጋር ንክኪ ኖራቸውም አልኖራቸውም “#ትግሬን ብቻ እየለዩ ነው።

እንግዲህ እነዚህ ድርጅቶች ስልጣን የያዘውም፣ ቢሳካለት ለመያዝ የሚፈልገውም የአማራን ህዝብ “#በወንጀለኝነት” የከሰሱ ናቸው።

ስልጣን የያዘው ብአዴን እርምጃውን የጀመረና በገፍ እያሰረ ሲሆን ስልጣን ያልያዘው ግ7 እና ደህሚት ምናልባት ከተሳካለት ከህወሃት የተረፈውን አማራ ልክ እንደ ህወሃት ለመጨፍጨፍና ቀሪውን የበቀል ማሰቃያ ቤት ለማጓጓዝ ተዘጋጅቷል ማለት ነው በመግለጫው መሰረት።በነገራችን ላይ ሰሞኑን ግ7 ወልድያ ላይ ወረቀት በትኛለው ባለ ምሽትና ማግስት ከ1ሺህ በላይ አማራዎች መታሰራቸው አይዘነጋም።

የአማራ ህዝብ ምን ማደረግ አለበት?

መፍትሄው የአማራ ህዝብ #ጠላቱ_ብዙ_መሆኑን_ማወቅና_ወቅት_እየጠበቀና_መላ_እየዘየደ_አምርሮ_መታገል ነው።ከራሱ ውጭ ማንም እንደሌለው መገንዘብ።

(ለማስረጃ ያህል በአማራ ተጋድሎ ወቅት ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎችን ከጎንደርና ከወሎ ትግሬ በመሆናቸው ብቻ አለመሆኑን የአማራ ክልል የባለፈው ሪፖርትና በዚህ ሳምንት ወሎ ላይ የተሰራውን ማጠቃለያ ተመልከቱና እናንተው ፍረዱ))

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.