ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች እጃቸውን ያስገቡ አካላትን የሚለይ የምርመራ ቡድን ስራ ጀመረ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/72042

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች እጃቸውን ያስገቡ አካላትን የሚለይ የምርመራ ቡድን ወደ ስራ ገብቷል

በተደራጀ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ሌብነትና፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተሳተፉ ሕገ-ወጦችን ወደ ሕግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡
ህግ የማስከበሩ ስርዓት አገሪቱ ላለችበት ለውጥ ወሳኝነቱ የጎላ በመሆኑ መንግስት ይህንን አካሔድ ተከትሎ ከሕግ ውጭ የሆኑ አካላትን የሚፈጽሙትን ተግባር የማይታገስና ለድርድር የማይቀርብ መሆኑንን ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች አቅደው ግጭቶችን በቀሰቀሱ ፣ለዜጎች ሞት፣ መፈናቀል፣ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት እያደረሱ የሚገኙ አካላትን ወደ ሕግ ለማቅረብ ችግሩ በተከሰተባቸው ሰፍራዎች የተደራጀ የምርመራ ቡድን በመላክ የምርመራዉ ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በቀጣይም የተገኙ ዉጤቶችን ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡
ህዝቡም ይህን እርምጃ በመደገፍና ከለውጡ ጎን በመሆን መንግስት እያካሄደ ያለውን የሕግና የፍትህ ማሻሻያ ስራ እንዲደግፍ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡
ወንጀል ፈጻሚ አካል የትኛውንም ብሔር፣ ሃይማኖት፣ጾታ ወዘተ የማይወክል መሆኑን ከግንዛቤ ውሰጥ በማስገባት በወንጀል ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሕግ እና በሕግ ሥርዓቱ ብቻ የሚዳኙ መሆናቸውንም የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.