ጎርፍ በዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የ45 ሰዎች ህይወትን ቀጠፈ

Source: http://www.yegnagudday.com/2018/01/12/%E1%8C%8E%E1%88%AD%E1%8D%8D-%E1%89%A0%E1%8B%B4%E1%88%9E%E1%8A%AD%E1%88%AB%E1%88%B2%E1%8B%AB%E1%8B%8A-%E1%88%AA%E1%8D%90%E1%89%A5%E1%88%8A%E1%8A%AD-%E1%8A%AE%E1%8A%95%E1%8C%8E-%E1%8B%A845-%E1%88%B0/

በዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለቀናት የጣለው ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ 45 ሰዎችን ገድሏል።

የአገሪቱ ቀይ መስቀል ማህበር እንዳስታወቀው ለቀናት የቆየ ዝናብ የቀጠቀጣት ዋና ከተማዋ ኪኒሻሳ በጎርፍ አደጋው 5 ሺህ ሰዎች ቤት አልባ ሆነውባታል።

ከሳምንት በፊት መጣል የጀመረው ሀይለኛ ዝናብ በከተማዋ ቤቶችን ያፈራረሰ ሲሆን፥ የመሬት መደርመስንም አስከትሏል።

የጎርፍ አደጋው አሁን አገሪቱን እያሰቃያት ያለው እና በ20 ዓመት ውስጥ የከፋ ነው የተባለውን የኮሌራ ወረርሽኝ ያባብሰዋል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት እስካሁን በኮሌራ ወረርሽኙ 1 ሺህ 190 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፥ የህዝብ ጥግግቱ በከፋባት ኪኒሻሳ መስፋፋቱ የከፋ ሆኗል።

12 ሚሊየን ህዝብ የሚኖርባት ኪኒሻሳ የማህበራዊ አገልግሎት መሰረተ ልማቷም እጅግ ደካማ ነው።

Share this post

Post Comment