ጎግል የምልክት ቋንቋን ወደ ንግግር የሚቀይር ቴክኖሎጂ መፍጠሩን አስታወቀ

Source: https://fanabc.com/2019/08/%E1%8C%8E%E1%8C%8D%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%88%9D%E1%88%8D%E1%8A%AD%E1%89%B5-%E1%89%8B%E1%8A%95%E1%89%8B%E1%8A%95-%E1%8B%88%E1%8B%B0-%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%8C%8D%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%89%80/

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል በስማርት ስልኮች አማካኝነት የምልክት ቋንቋን በማንበብ ወደ ድምጽ ንግግር የሚቀይር ቴክኖሎጂ መፍጠሩን አስታውቋል።

ጎግል የምልክት ቋንቋን የሚያነብ መተግበሪያ በራሱ ያልሰራ ቢሆንም፥ የመተግበሪያ አልሚዎች ግን በቀላሉ ሊሰሩበት የሚችሉበትን ቀመር ይፋ መድረጉም ነው የተገለፀው።

እስካሁን የዚህ አይነት ሶፍትዌሮች በኮምፒውተሮች ላይ ብቻ የሚሰራ እንደነበረ ነው የተነገረው።

ጎግል አሁን ይፋ ያደረገው ቴክኖሎጂም በተለይም መስማት በተሳናቸው ማህበረሰቦች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱም ነው የተነገረው።

የጎግል የምርምር ኢንጂነር የሆኑት ቫሌቲን ባዜርቪስኪ እና ፋን ዘሃንግ እንዳስታወቁት፥ ቴክኖሎጂውን በነፃ ይፋ የማድረግ ዋነኛው አላማም ሰዎች በቀላሉ የምልክት ቋንቋን እንዲረዱ ለማድረግ ካለ ፍላጎት የመነጨ ነው።

አሁን ከሰዎች እየተገኘ ባለው ምላሽ ደስተኞች መሆናቸውን እና በቀጣይም ጎግል ቴክኖሎጂውን የበለጠ ለማበልፀግ እንዲሁም ሁሉንም የምልክት ቋንቋዎች ወደ ድምጽ የመቀየር ስራውን አጠናክረው እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ www.bbc.com

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.