ጠቅላይ ሚኒስትሩም ኦዴፓም ኪሳራ እንዲደርስባቸው ተብለው የተሰሩ ስራዎች አሉ – አቶ ታዬ ደንደአ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/170033

“አምቦ የፖለቲካ ስዕሉ ትልቅ ስለሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ኦዴፓም ኪሳራ እንዲደርስባቸው ተብለው የተሰሩ ስራዎች አሉ። ይህ ተጣርቷል፤ ህብረተሰቡም አውቋል” አቶ ታዬ ደንደአ የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል
*********************************
ዋና ዋና ሃሳቦችን
• ተረኝነት የሚባለው በየትኛውም ብሄር በየትኛውም ፓርቲ ሌባም፣ ሙሰኛም ባለጌም፣ ቀጣፊ፣ አሰመሳይ ይኖራል።በዚህ ደረጃ አንዳንድ የተረኝነት ስሜት የተቆራኛቸው አባላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገምታል። ግን በፓርቲ ደረጃ የለም።
Image may contain: 1 person, sitting

• ኦዴፓ እንደ ፓርቲ ለውጡንም የኦሮሞ ህዝብ ብቻውን አመጣ አይልም። የኦሮሞ ህዝብ ትልቅ ሚና መጫወቱ ይታወቃል፤ ያንን እናምናለን።ቢሆንም ብቻውን የመጣውን ለውጥ ማምጣት አይችልም ነበር።
• የኦዴፓ አመለካከት በፊት ከነበረው ይልቅ የበለጠ አገራዊ ብቻም ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካም ደረጃ ያደገ አስተሳሰብ ያለው ፓርቲ ነው።
• ኦዴፓ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ለማስከበር ሲታገል ሌላውን ወደ ጎን የሚገፋ ኢትዮጵያንም የሚረሳ አይደለም።
• በዚህ ለውጥ ውስጥ ታሪክም ስለሆነ የኦሮማራ ጉዳይ መርሳት አያስፈልግም። ኦሮማራ ይሄን ለውጥ ወደፊት ከመውሰድ፤ መስመር ከማስያዝ፤ ለለውጡ ሀይል አቅም ከመፍጠር አንጻር ትልቅ ሚናን ማንም ሊክደው ሊሽረው የማይችለው አቅም ፈጥሯል።
• በጥላቻ ላይ፣ በትናንት ታሪክ ላይ ተቸንክረን እሱን እየመነዘርን፤ አንዱ ወደ አንድ አቅጣጫ ሲጎትት ሌላው ወደ ሌላ አቅጣጫ እየጎተተ እሱን ብቻ እያኘክን መኖር አለብን የሚል ስሜት የለኝም። እንዲህ ያለው አካሄድ ድፍረት ይጠይቃል፤ ለስድቦችና ለሌሎች ነገሮች እንደምትጋለጥ አውቀህ ችሎ መቆምን ይጠይቃል።
• ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ሌላ አማራጭ የላትም፤የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ሕዝብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ሌላ አማራጭ የለውም፤ኢህአዴግን ማሻሻል

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.