ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቦንጋ ከነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/09/%E1%8C%A0%E1%89%85%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%8B%B6%E1%8A%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8B%90%E1%89%A2%E1%8B%AD-%E1%8A%A0%E1%88%85%E1%88%98%E1%8B%B5-%E1%89%A6/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ቦንጋ ከተማ ከነዋሪዎች ጋር በመወያየት ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ማኒስትሩ ከካፋ ዞን ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነው እየተወያዩ የሚገኙት ።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣  የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳም በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅድሚያ ሊቀበሏቸው በከተማዋ ስታዲየም ለተሰበሰበው የከተማዋ ነዋሪዎች ንግግር አድረገዋል።

በውይይቱ ነዋሪዎቹ በክልል ከመደራጀት፣ ከመሰረተ ልማት እና  ከጤና ተቋም ግንባታጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፥ ዞኑ ካለው እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ እንዲሆን ኢንቨስትመንት እንዲመጣም ጠይቀዋል።

 

በአልአዛር ታደለ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.