ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቻይና ከሚገኙ የተለያዩ ኩባንያዎች ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

Source: https://fanabc.com/2019/04/%E1%8C%A0%E1%89%85%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%8B%B6-%E1%88%AD-%E1%8A%A0%E1%89%A5%E1%8B%AD-%E1%8A%A0%E1%88%85%E1%88%98%E1%8B%B5-%E1%89%A0%E1%89%BB%E1%8B%AD-2/

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቻይና ከሚገኙ የተለያዩ ኩባንያዎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

በውይይቶቹ ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ እያከናወኑት ስለሚገኙት ኢንቨስትመንት ተወያይተዋል።

ከመሰረተ ልማት ግንባታ አንስቶ እስከ አምራች ዘርፍ ድረስ በተለያዩ ዘርፎች ላይ መሰማራት እንደሚፈልጉ የየኩባንዎቹ ሃላፊዎች ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ ከቻይና ሬልዌይ ኮርፖሬሽን (ሲአርሲሲ )ሃላፊዎች  ጋር ባደረጉት ምክክር ከቀናት በኋላ በሚካሄደው የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤና ተያይዘው በሚነሱ ፕሮጀክቶች ዙሪያ መክረዋል።

ኩባንያው ከሚያከናውናቸው ግዙፍ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መካከል የቤልት ኤንድ ሮድ ማእቀፍ አካል የሆነው የኢትዩ ጅቡቲ ባቡር መስመር ግንባታ ፕሮጀክት አንዱ ነው።

ኩባንያው በተጨማሪም በአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታና በማእድን ዘርፍ በተለይም የነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ማምውጣት ስራ ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ይፋ ተደርጓል።

የሲ አር ሲ ሲ ኩባንያ በሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ እንደሚፈልግም አስታውቃል።

 

በሰላማዊት ካሳ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.