ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2018 የአፍሪካ ምርጥ ሰው ሽልማትን አሸነፉ

Source: https://fanabc.com/2018/12/%E1%8C%A0%E1%89%85%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%8B%B6-%E1%88%AD-%E1%8A%A0%E1%89%A5%E1%8B%AD-%E1%8A%A0%E1%88%85%E1%88%98%E1%8B%B5-%E1%8B%A82018-%E1%8B%A8%E1%8A%A0/

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአፍሪካን ሊደርሺፕ መጽሔት  የ2018 የአፍሪካ ምርጥ ሰው የሚል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በ7 ዘርፍ ተከፋፍሎ በተካሄደው እና ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ድምጽ በሰጡበት በአፍሪካን ሊደርሺፕ መጽሔት ውድድር ነው የዓመቱ አፍሪካዊ ምርጥ ሰው ሽልማትን ያሸነፉት።

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተሰጠው ድምፅ ከ85 በመቶ በላይ በማግኘት የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ሰው የሚለውን ሽልማት አሸናፊ መሆን ችለዋል።

የአፍሪካን ሊደርሺፕ መጽሔት  የሰባቱም ዘርፍ አሸናፊዎች ዝርዝርም፡-

  • የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፦ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ
  • ናይጀሪያዊቷ የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄ መሀመድ፦ የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ ሴት መሪ
  • ናይጀሪያዊው መሀመድ ኢንዲሚ፦ በትምህት ዘርፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ
  • ናይጀሪያዊው አቲኩ አቡበከር፦ የዓመቱ አፍሪካዊ ምርጥ ሥራ ፈጣሪና ቀጣሪ
  • የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ፦ በፖለቲካዊ አመራር የዓመቱ ምርጥአፍሪካዊ
  • ናይጀሪያዊው ቶኒ ኢሉሜሉ፣ ሄይርስ ሆልዲንግ፦ በበጎ አድራጎትና ለማኅበረሰብ ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከት የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ
  • የቦትስዋናው የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቦጎሎ ጆይ ኬንወንዶ፦ የዓመቱ አፍሪካዊ ምርጥ ወጣት

የውድድሩ አሸናፊዎች በመጪው የካቲት ወር አጋማሽ በደቡብ አፍሪካ ጁሀንስበርግ በሚካሄድ ስነ ስርዓት ሽልማታቸውን እንደሚቀበሉም አፍሪካን ሊደርሺፕ መጽሄት አስታውቋል።

Share this post

One thought on “ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2018 የአፍሪካ ምርጥ ሰው ሽልማትን አሸነፉ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.