ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፍራንክፈርት ኮሜርዝ ባንክ አሬና ስቴድየም ለኢትዮጵያውያን ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች

Source: https://mereja.com/amharic/v2/63790

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፍራንክፈርት ኮሜርዝ ባንክ አሬና ስቴድየም ለኢትዮጵያውያን ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-
• ሀገራችን ከአውሮፓውያን ጋር ከጥንት ጀምሮ የቆየ ታሪካዊ ትስስር አላት፡፡ ይህ ለዛሬው ግንኙነታችን መሰረት ጥሏል፡፡
• ጀርመናውያን በዓለም ጦርነት ወድማ የነበረችውን ሀገራቸውን መልሰው ለመገንባት የወሰደባቸው ከ40 ዓመታት ያልበለጠ ጊዜ ነው፡፡
• አውሮፓውያን እርስ በርስ ከመሸናነፍ ይልቅ ድህነትን ማሸነፍን በመምረጣቸው ዛሬ እዚህ ደርሰዋል፡፡ ይህ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ትምህርት ይሰጠናል፡፡
• ዛሬ ያላየነውን የምናይበት ያልሞከርነውን የምንሞክርበት ጥርሳችንን ነክሰን የምንሰራበት ወቅት ነው፡፡
• ኢትዮጵያ ማንም በየጊዜው እየተነሳ እንደ ቂጣ ጠፍጥፎ የሚሰራት የግል ርስት ሳትሆን ዘመናትን ያስቆጠረች ታላቅ ህዝብ የመሰረታት ታላቅ ሀገር ናት፡፡
• “እሳት ቢያንቀላፋ ገለባ ጎበኘው” ዓይነት ሊደርጓት ለሚሹ – ኢትዮጵያ አንቀላፍታ ደክማ ይሆናል እንጂ አልሞተችም፤ ቀጥናለች እንጂ አልተበጠሰችም፡፡
• ኢትዮጵያዊነትን ከስሜት በዘለለ በስራ የምንገልፅበት ወቅት ላይ ነን፡፡
• ከትናንት አያሌ መልካም ነገሮች እንደወረስን ሁሉ ብዙ መለወጥ ያለባቸውም አሉ፡፡
• ዛሬንና ነገን ጥሩ የምናደርገው ስለትናንት በመነታረክ አይደለም፡፡
• እኔ ለሀገሬ ምን ሰራሁ እንጂ እነእገሌ ሀገሬን ጉድ ሰሯት ከማለት ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡
• ጠንክረን ካልሰራን ፍትሕና ዴሞክራሲ እንዲሁ አይመጣም፡፡ ተደምረን ተግተን ስንሰራ ብቻ ነው ይህ እውን ሊሆን የሚችለው፡፡
• ለዚሁ ዓላማ ተቋማትን በመገንባት ኃላፊነታቸውንም በአግባቡ የሚወጡ ሰዎች በመመደብ ላይ እንገኛለን፡፡
• በምርጫ ቦርድ፣ መከላከያ፣ ፍትሕ፣ ትምህርት ወዘተ ተቋማት አስፈላጊውን ማሻሻያ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡
• በቅርቡ በፍትሕ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.