ጠ/ሚር አብይ የሰጠኸኝን ጥሩ ሀሳብ ባለመቀበሌ የለውጡ እንቅፋት ነበርኩ።ለዚህም ከልቤ ተፀፅቻለሁ። አቶ አብዲ መሀመድ ኢሌ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/64153

 
የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት እና አሁን በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አብዲ መሀመድ ኡማር ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ጥቅምት 14 የፃፉትን ደብዳቤ ሰሞኑን ለማግኘት ችዬ ነበር። ካሉት ዋና ዋናዎቹ:

* በክልሉ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ እና ንብረት እንዳይወድም አንተ (ጠ/ሚር አብይ) የሰጠኸኝን ምክር እና ሀሳብ ችላ ብያለሁ።
* እንደገናም ችግሩ ከተከሰተ በሁዋላም ሳትተወኝ የሰጠኸኝን ጥሩ ሀሳብ ባለመቀበሌ የለውጡ እንቅፋት ነበርኩ። ለዚህም ከልቤ ተፀፅቻለሁ።
* አሁንም ቢሆን ቃልህን እንደማታጥፍ እና ፊትህን እንደማታዞርብኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
* ከመጀመርያ ጀምሮ አመጣጥህንና እያመጣህ ያለውን አመርቂ ለውጥ በጣም አደንቃለሁ።
* እኔም ስህተቴን አርሜ ከህዝብ እና መንግስት ጋር በመሆን የለውጡ ቸርኬ ሆኜ እሰራለሁ።
ELIAS MESERET

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.