ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ ከሪፑብሊኩ የጥበቃ ኃይል አባላት ጋር ተገናኙ፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/77608

ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ ከሪፑብሊኩ የጥበቃ ኃይል አባላት ጋር ተገናኙ፡፡

የሪፑብሊክ የጥበቃ ኃይል አባላትም የመንግስት ባለስልጣኖች እና ቤተሰቦቻቸውን የጥቃት ዓላማን አንግበው ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከሚሰነዘር ጠለፋና እንግልት ለመከላከልና ለማዳን ዝግጁነታቸውን የሚያሳይ ትርዒት አቅርበዋል፡፡
የሪፑብሊክ የጥበቃ ኃይሉ የአገሪቱን ሕገ-መንግሥትና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በአዲስ የተቋቋመ የደኅንነት መሣሪያ አካል ነው፡፡ ይህ የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል በከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ያሉትን ኃላፊዎች ከማንኛውም ስጋት እና ጥቃቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዘዴ መጠቀም ዋነኛ ተግባሩ ነው፡፡
ባለፉት 6 ወራትም ይህ ኃይል እራሱን በሰለጠኑ የደኅንነት ባለሙያዎችና በተገቢው መንገድ ተግባሩን ለማከናወን የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን እያደራጀና ስልጠናዎች እያደረገ ቆይቷል፡፡ የዛሬው ትርዒትም ማናቸውም ጥቃቶችን ለማስቆምና ለመመከት ያለውን ዝግጁነትና ሙሉ አቅሙን ለማሳየት የተዘጋጀ ነው::
ምንጭ።፦ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ.ቤት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.