ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች

Source: https://mereja.com/amharic/v2/57820

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፡-
• ከእንግዲህ ትኩረታችን ወጣቱን የስራ ባለቤት ማድረግ ነው፡፡
• ፊታችንን ወደ ስራ ለማዞር የማብሰሪያው ዕለት ነው ዛሬ፡፡
• የልማት እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ ማድረግ የመንግስት ዋነኛው ስራ ነው፡፡
• የኢንዱስትሪ ልማት ሲስፋፋ ቦታው ለትራንስፖርት ምቹ መሆኑ ይታያል፤ አዳማን የሚያህል ምቹ ስፍራ የለም፤ የባቡር መስመር፣ ፈጣን መንገድ፣ ወደፊት ከአዳማ በቅርብ ርቀት የሚሰራው ትልቁ የአየር ማረፊያ ከተማዋን ተመራጭ ያደርጓታል፡፡
• የአዳማ ወጣትና ነዋሪ ላለፉት ጊዜያት በተካሄደው ትግል ካለአንዳች ጥፋት ተቃውሞውን በሰላማዊ መንገድ ሲገልፅ የቆየ ነው፡፡
• የባለሀብቶች ዋነኛው ጥያቄ መንገድ አለ ወይ ሳይሆን ሰላም አለ ወይ በመሆኑ ሰላማችሁን መጠበቃችሁን አትዘንጉ፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.