ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከኖርዌይ አቻቸው ኤርና ሶልበርግ ጋር ተወያዩ

Source: https://fanabc.com/2019/12/%E1%8C%A0-%E1%88%9A-%E1%8B%90%E1%89%A2%E1%8B%AD-%E1%8A%A0%E1%88%95%E1%88%98%E1%8B%B5-%E1%8A%A8%E1%8A%96%E1%88%AD%E1%8B%8C%E1%8B%A9-%E1%8A%A0%E1%89%BB%E1%89%B8%E1%8B%8D-%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%8A%93/

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኖርዌይ አቻቸው ኤርና ሶልበርግ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅትም ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን በማጠናከር እና የተጀመረውን የለውጥ ሂደት በማስቀጠል ላይ እያከናወነች ባለው ስራ ላይ መክረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ወቅትም የኢትዮጵያን የባህር ኃይል በአቅም ግንባታ ድጋፍ ለማጠናከር፣ ኢትዮጵያውያን ሴት አመራሮች በፖለቲካ አመራር ላይ ልምድ እንዲለዋወጡ ለማስቻልና የእውቀት ሽግግር ለማካሄድ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ ላይ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኖርዌይ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ቶን ትሮን እና በአኒከን ሁይትፊል ከሚመራው የውጭ ጉዳይና መከላከያ ቋሚ ኮሚቴ ጋርም ተወያይተዋል።

ውይይቶቹም በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ባሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.