ጠ/ሚ ዐቢይ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው የሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና በአፍሪካ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ሲሪል ራማፎሳ የአፍሪካ ህብረትን የወቅቱ ሊቀመንበርነት ተረክበው መንቀሳቀስ ከጀመሩ አንስቶ ፤ የአፍሪካ ጉዳዮች በአፍሪካውያን እንዲፈቱ እያደረጉት ላለው ጥረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለፕሬዚዳንቱ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡

The post ጠ/ሚ ዐቢይ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply