ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኳታር ገቡ

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%8C%A0-%E1%88%9A-%E1%8B%B6%E1%8A%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8A%A0%E1%89%A5%E1%8B%AD-%E1%8A%A0%E1%88%85%E1%88%98%E1%8B%B5-%E1%88%88%E1%8B%AD%E1%8D%8B%E1%8B%8A-%E1%8B%A8%E1%88%B5%E1%88%AB-%E1%8C%89/

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኳታር ገብተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን ዶሃ ሲደርስ የኳታር የትራንስፖርት እና መገናኛ ሚኒስትር ጃሲም ቢን ሳይፍ አል ሱለይቲ አቀባበል አድርገውለታል።

በቆይታቸውም ከሃገሪቱ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር በሁለትዮሽና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም ወደፊት በሚተገበሩ የጋራ በሆኑ የልማት ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎም ነው የሚጠበቀው።

የኢትዮ ኳታር ግንኙነት እየተሻሻለ ሲሆን፥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝትም የሃገራቱን ግንኙነት ወደተሻለ የትብብር ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ታምኖበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የመጀመሪያቸው የሆነው ጉብኝት፥ ለሃገራቱ ግንኙነት መሻሻል ካለው ፋይዳ አንጻር ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑም ተገልጿል።

የኳታሩ ኤሚር በኢትዮጵያ ከሁለት አመት በፊት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፥ የየሃገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትም በተለያየ ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያግዙ ጉብኝቶችን አካሂደዋል።

ከባለስልጣናቱ ጉብኝት ባለፈም ሃገራቱ በተለያዩ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችሉ የመግባቢያ ስምምነቶችን ፈጽመዋል።

ኢትዮጵያም በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ የኳታር ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለፈው ጥር ወር በዶሃ በኢትዮጵያ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማሳየት ያለመ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፎረም ተካሂዶ በር።

ፎረሙ በተያዘው የፈረንጆቹ አመት በተለያየ ጊዜ ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፥ ይህም የሃገራቱን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከርና ለማሳደግ ያስችላል ተብሏል።

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.