ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ከተሰናባቹ የኢጋድ ዋና ፀሀፊ አምባሳደር ማህቡብ ማሊም ጋር ተወያዩ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8C%A0-%E1%88%9A-%E1%8B%B6%E1%8A%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8B%90%E1%89%A2%E1%8B%AD-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%B0%E1%8A%93%E1%89%A3%E1%89%B9-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%8C%8B%E1%8B%B5-%E1%8B%8B%E1%8A%93/

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከተሰናባቹ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ አምባሳደር ኢንጂነር ማህቡብ ማሊም እና ከአዲሱ ዋና ጸሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ማሊም ለክፍለ አሕጉራዊው ድርጅት እና ቀጠናውን ለማረጋጋት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።

ኢጋድ በትናንትናው እለት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዋና ፀሃፊ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።

 

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው።

Share this post

One thought on “ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ከተሰናባቹ የኢጋድ ዋና ፀሀፊ አምባሳደር ማህቡብ ማሊም ጋር ተወያዩ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.