ጳጉሜን 6 የብሄራዊ አንድነት ቀን ሆኖ ታስቦ ይውላል

Source: https://fanabc.com/2019/08/%E1%8C%B3%E1%8C%89%E1%88%9C%E1%8A%95-6-%E1%8B%A8%E1%89%A5%E1%88%84%E1%88%AB%E1%8B%8A-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%89%80%E1%8A%95-%E1%88%86%E1%8A%96-%E1%89%B3%E1%88%B5%E1%89%A6/

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ‘ጳጉሜን በመደመር’ ሀገራዊ መርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የመደመር ስድስት ምሰሶወችን የሰነቀ ጳጉሜን በመደመር ሀገር አቀፍ መርሃ ግብር እየተካሄደ እንደሚገኝ ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡

የተለያዩ የመንግስት አካላት የየዕለት እንቅስቃሴዎቹን ለማቀድ ፣ ለመምራት፣ ለማስተባበር እና ለማስፈፀም ሀላፊነት ወስደው የተለያዩ ተግባራትን እየፈፀሙ ይገኛል፡፡

በዚህም የጳጉሜን ስድስቱ ቀናት ስያሜ እና አስተባባሪዎች ይፋ ሆነዋል፡፡

ጳጉሜን 1 ብልፅግናን የወከለ ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያስተባብረዋል፡፡

ጳጉሜን 2 ደግሞ የሰላም ቀን የተባለ ሲሆን በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፊሪያት ካሚል እንደሚመራ ነው የተገለፀው፡፡

ጳጉሜን 3 ሀገራዊ ኩራት የሚል ስያሜን በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተሰጥቶዋቸል፡፡

ጳጉሜን 4 ዲሞክራሲ የሚል ስያሜን በትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተሰጠ ሲሆን ዕለቱን በአስተባባሪነት የሚመሩ ይሆናል፡፡

ጳጉሜን 5 ደግሞ የፍትህ ቀን ሆኖ እንዲታሰብ በፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋየ ተስይሟል፡፡

እንዲሁም የመጨረሻው እና የአዲስ አመት ዋዜማው ጳጉሜን 6 የሀገራዊ አንድነት ቀን ሆኖ ታስቦ እንዲውል ነው የተወሰነው፡፡

ህብረተሰቡም በእነዚህ ቀናት ሰፊ ተሳትፎ በማድረግ ወደ መጪው አዲስ አመት ተስፋን ሰንቆ ለመሻገር ይሁንልኝ ብሎ እንዲሰራ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.