ጸረ- አማራ ቡድኖችን በአንድነት ያሰለፈው የወሎ አማራ ህዝባዊ ንቅናቄ

Source: http://welkait.com/?p=12022
Print Friendly, PDF & Email

(By Yohannes Amhara)

ከጥቅምት 25 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለባለፉት 2 ወራት የወሎ አማራ ህዝብ ጸረ-ህዋሃት ህዝባዊ ተጋድሎ ላይ ነው። የመቀሌ እና የወልድያ እግርኳስ ቡድኖች በነበራቸው ግጥሚያ የህዋሃት እብሪተኞች የአማራ ህዝብን በመዝለፋቸው የተነሳ የወልድያ ህዝብ ተቆጥቶ የተጀመረው ህዝባዊ እምቢተኝነት እስካሁን ድረስ አልበረደም።

በህዝባዊ ትግሉ ከ50-70 የሚደርሱ አማራዎች መስዋዕት ሆነዋል፤ ከ600 በላይ ወጣቶች እና ባለሃብቶች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በወልድያ ስታዲየም፤ በአፋር ክልል ጭፍራ በተባለ ቦታ እና በትግራይ እስር ቤቶች ታጉረው ግርፋት እና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። እስር እና አፈናው እንዲሁም ድብደባ እና እንግልቱ እስከዚህች ደቂቃ ድረስ አልቆመም።

ይህ ለነጻነት እና እኩልነት የሚደረግ ህዝባዊ ተጋድሎ ልዩ የሚያደርገው ከባድ መስዋዕትነት ማስከፈሉ ብቻ ሳይሆን ከመቀሌ እስከ ባህርዳር፤ ከዲሲ እስከ አስመራ እና አዲስ አበባ ድረስ ያሉ ጸረ አማራ ቡድኖች በአንድ ላይ ተሰልፈው የተከበረውን የወሎ ህዝብ በተናጠል እንዲሁም አጠቃላይ የአማራን ህዝብ በጅምላ የጨፈጨፉበት እና ያወገዙበት መሆኑ ነው።

ይደንቃል..በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ተቃዋሚዎችም (ግንቦት ሰባት እና ደምሂት) ሆነ ገዥዎች ( ብአዴን፤ ህዋሃት) በአንድ ላይ የተነሱበት ህዝብ ቢኖር አማራ ብቻ ነው።

ብአዴን

በአለምነው መኮነን የሚመራው እና ክልሉን አስተዳድራለሁ የሚለው ብአዴን ቁጥር አንድ ጸረ- አማራ ቡድን መሆኑን ያስመሰከረው በተለየ መልኩ በሰሞኑ ህዝባዊ እምቢተኝነት ነው ማለት ይቻላል። ብአዴን ከአለቃው ከህዋሃት የሚሰጠውን አረመኒያዊ ትዕዛዝ ሳይሸራርፍ በመተግበር የወሎ አማራዎችን በጅምላ አዋክቧል፤ ሰልሏል፤ አስሯል፤ አሳፍኗል፤ ገድሏል፤ አስገድሏል። እንደ ኦህዴድ ተሻሽሎ ለአማራ ህዝብ ጥብቅና ሊቆም ይችላል ተብሎ የታሰበውን ገደል በመክተት ቁጥር አንድ አረመኔ እና ርህራሄ አልባ ተላላኪ ቡድን መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ከ70 በላይ የተሰው የአማራ ነፍሶች ሳይሆን በሌብነት እና ዝርፊያ ተገኝቶ የተገነቡ የህዋሃት ሰላዮች ፎቆች እንደሚያሳስቡት እና የአፈና ርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በግልጽ ቋንቋ ነግሮናል። እናም ድርጅቱ አማራን ከማጥፋቱ በፊት ራሱ ከምድረገጽ መጥፋት እንዳለበት አስተምሮን አልፏል።

ህዋሃት

ሌላው ቁጥር አንድ ጸረ-አማራ ቡድን ያው የታወቀው ህዋሃት ነው።ከ1968 ዓ.ም. ጀምሮ አማራን ለማጥፋት ቀን ሌሊት የሚለፋው ይህ የትግራይ ገዥ ቡድን ምህረት የለሽ አጋዚ ወታደሮችን ወደ ሰሜን ምስራቅ አማራ ልኮ በወልድያ፤ ቆቦ፤ መርሳ፤ ሲሪንቃ እና ሌሎች ከተሞች ላይ ጅምላ ግድያ በመፈጸም መተከያ የሌለውን የብዙ አማራዎችን ህይወት ያለ ርህራሄ ቀጥፏል። እሱ ብቻ አይደለም። ከአሽከሩ ብአዴን ጋር በመተባበር ከወልድያ፤ መርሳ እና ቆቦ ወጣቶችን በማፈስ ወደ ትግራይ እና አፋር እርስቤቶች እንዲሁም ማሰቃያ ስፍራዎ ች በመውሰድ በሰው ልጅ ላይ ይደረጋሉ ተብለው የማይታሰቡ አረመኒያዊ ድርጊቶችን እየፈጸመ ነው።

ግንቦት ሰባት

ይህ ቡድን ቀጥር አንድ ጸረ-አማራ ቡድን ነው ማለት ከጀመርን እነሆ 4 አመታትን ልናስቆጥር ነው። ያኔ የሚሰማን አልነበረም። ደግነቱ ጊዜ መስታወት ሆኖ የግንቦት ሰባት ጸረ አማራነት በተግባር ከቀን ወደ ቀን ግልጽ እየሆነ ነው። ድርጅቱ በጎንደር እና ጎጃም እንዲሁም ወሎ በተደረጉት ህዝባዊ ተጋድሎዎች ላይ እጄ አለበት እያለ እና በራሪ ወረቀቶችን እየበተነ ህዝባችንን የህዋሃት እሳት ራት እያደረገ ያለ ቡድን ነው። ጭራሽ ይባስ ብሎ መተኪያ የሌለውን ህይወታቸውን አሳልፈው ከሰጡ የአማራ ወጣቶች ይልቅ የህዋሃት ሰላዮች ንብረት መውደም አሳስቦት “የበቀል እርምጃ እየተወሰደባቸው ካሉ የህወሃት ካድሬዎች በተጨማሪ ከህወሃት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልነበራቸው ሰዎችም የጥቃቱ ሰልባ እንደሆኑ መስማት እየተለመደ መጥቶአል“ ስለሆነም ትግራይን አትግደሉ” ሲል ለአለቃው ሻዕቢያ እና ለወዳጁ ደምሂት ያለውን አጋርነት እንዲሁም ለሰፊው የአማራ ህዝብ ያለውን ወደር ያልተገኘለት ጥላቻ በማያሻማ ቋንቋ የነገረን ቡድን ነው። ይህ ቡድን መተኮሻ መሳሪያ ባይኖረውም በሚያሳራጫቸው የተዛቡ መረጃዎች እና ፕሮፓጋንዳዎች የተነሳ የብዙሃን አማራዎችን ህይወት የቀጠፈ እና ያስቀጠፈ ከህዋሃት እና ከብአዴን ጋር ከምድረገጽ መጥፋት ያለበት ድርጅት ነው።

ደምሂት

ስለዚህ ቡድን ምን ማለት ይቻላል? ከ20 ሺህ በላይ ሰራዊት ገንብቶ ነገር ግን አንድም ቀን አንዲት ጥይት እንኳ ወደ ወያኔ መተኮስ የማይፈልግ ድርጅት ሲሆን ከግንቦት ሰባት ጋር በገባው ውል መሰረት “ወልቃይት የትግራይ ነው” ብሎ የሚያምን ጸረ-አማራ ቡድን ነው። ከዚህ በተጨማሪም በግንቦት ሰባት ውስጥም ይሁን በሌሎች ኤርትራ መሽገው በሚገኙ ሃይሎች ውስጥ የሚታገሉ የአማራ ልጆችን በማሳፈን፤ እንቅስቃሲያቸውን ለሻዕቢያ እና ህዋሃት መረጃ በማቀበል እንዲሁም በስውር በማስገደል እጁ በደም የተጨማለቀ ቡድን ነው። ድርጅቱ ኢትዮጵያዊ ስሜት ቢኖረው ኖሮ በአማራ ህዝብ ላይ ለባለፉት 2 አመታት የታወጀውን መጠነ ሰፊ እልቂት በማውገዝ ከጭቁኖች ወገን መሰለፍ ይገባው ነበር..ነገር ግን ትግሬ ህዋሃት የተጠቃ ሲመስለው እውነተኛ ቀለሙን ይዞ ብቅ አለ። የዚህ ቡድን የውጭ ሃገር ዲፕሎማሲ ስራውን የሚያከናውነው በቀድሞው የህዋሃት ታጋይ በዶክተር አረጋዊ በርሄ አማካኝነት ሲሆን ሰውየው ከእነ ብርሃኑ ነጋ እና ሌንጮ ለታ ጋር በፖለቲካዊ ሽርሙጥና አንሶላ የሚጋፈፍ ሳር ውስጥ ያለ እባብ ነው።

ሲጠቃለል

======
የወሎ አማራ ህዝብ ተጋድሎ እኒህን ጸረ-አማራ ቡድኖችን እና ግለሰቦችን በአንድ ላይ ያሰለፈበት ምክንያት አንድ እና አንድ ነው..እንቅስቃሴው ሙሉ በሙሉ በአማራዊ ስሜት የተቃኘ ብሎም ዘር እና ሃይማኖት ሳይለይ የስርአቱ አገልጋዮች በተባሉት ላይ በሙሉ መጠነ ሰፊ ውድመት በማድረሱ ነው። ነገር ግን እልፍ አእላፍ ጠላቶች ከአማራ ህዝብ በተቃራኒ ቢሰለፉ እንኳ ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው እና አንበረከክም። እድሜ ለአማራ ብሄርተኝነት እና ለአዲሱ የግዮን ትውልድ ይሁን እና ጠላታችን ማን እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን፤ መዳኛችን ምን እንደሆነም እንዲሁ አሳምረን እንረዳለን፤ እናም ትግሉን እስከ ቀራኒዮ ድረስ እንገፈዋለን..ጸረ – አማራ ቡድኖች እና ግለሰቦችም በታሪክ ፊት ራሳቸውን አዋርደው እንደ ጉም ትን ብለው ይጠፋሉ!

#ድል #ለሰፊው #የአማራ #ህዝብ
ሞት ለጸረ- አማራ ቡድኖች በሙሉ!

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.