ፋሲል ከነማ 50 አመት ይዞት የኖረውን የክለቡን ስያሜ ቀይር መባሉ ተቃውሞ አስነሳ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/147260

ፓለቲካዊ ይዘት ያለው የፋሲል ከነማ ስያሜ ሳይሆን የፌዴሬሽኑ ጥያቄ ነው !
ፋሲል ከነማ ለጎንደር ህዝብ መገለጫው ነው የዛሬ 50 አመት የነበረን ስያሜ ዛሬ ቀይሩ ማለት መልእክቱ ሌላ ነው
የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ ስያሜ ከዛሬ አምሳ አመት በፊት የነበረ አንጋፋ የጎንደር ህዝብ መገለጫ ህዝባዊ ክለብ እንጅ በፓለቲካዊ ስያሜ የተቋቋመ የስፓርት ክለብ አይደለም ፌዴሪሽኑ ውሳኔውን መለስ ብሎ ሊመለከት ይገባል።

ፋሲል ከነማ ራዕዩ ሕልም እና አቋሙ ስፖርት ብቻ ነው!! ስያሜውም የጎንደር ከተማ መገለጫ በሆነው በዮኔስኮ በተመዘገበው የኢትዮጵያ ቅርስ ፋሲል ግንብ አሰሪ እና የኢትዮጵያ ንጉስ በሆኑት በአፄ ፋሲለደስ የተሰየመ እንጂ ሌላ ፓለቲካዊ አጀንዳ ያለለው ፍፁም ኢትዮጵያዊ ክለብ ነው ፋሲል ከነማ ።
የጎንደር ከተማ ህዝብና የክለቡ ደጋፊዎችም ይህንን የፌዴሬሽን ውሳኔ እንደማይቀበሉት ፌዴሬሽኑ ያውቃል ነገር ግን ፌዴሬሽኑ ከጀርባ የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብን በእንደዚህ አይነት ነገሮች ችግር ውስጥ በማስገባት የስፓርት ክለቡን አንገት ለማስደፋት የሚደረግ ፓለቲካዊ አንድምታ ያለው ውሳኔ ነው ።
ፓለቲካዊ ይዘት ያለው የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ ስያሜ ሳይሆን የፌዴሬሽኑ ድፍረት የተሞላበት ስም ቀይሩ ውሳኔ ነው ይህን ደግሞ መላው ኢትዮጵያዊ ስፓርት ወዳጅ እና የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በፅኑ የምንቃወመው ውሳኔ ነው ።#MinilikSalsawi

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.