‹‹ፌዴራሊዝም የአስተዳደር ዘይቤ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ተስፋም ስጋትም አይደለም፤ ችግሩ አተገባበሩ ላይ ነው፡፡›› ምሁራንና ፖለቲከኞች

Source: https://mereja.com/amharic/v2/74423

‹‹ፌዴራሊዝም የአስተዳደር ዘይቤ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ተስፋም ስጋትም አይደለም፤ ችግሩ አተገባበሩ ላይ ነው፡፡›› ምሁራንና ፖለቲከኞች
(አብመድ) የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የሥራ አስፈጻሚ አባል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ‹‹ፌዴራሊዝም የሀገራችን የረዥም ጊዜ የሕዝብ ጥያቄ ያመጣው አደረጃት ነው›› ብለዋል፡፡
እንደ ፕ.ር መረራ የንጉሡም ሆነ የደርግ ሥርዓቶች የሕዝብን መብት አፍነው ስለነበር በ1960ዎቹ ከመሬት ላራሹ ቀጥሎ ይነሳ የነበረው ጥያቄ የብሔር ብሔረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ነው፡፡ ‹‹የረዥም ዘመን የሕዝቦችን ጥያቄ ለመመለስ ኢህአዴግ ወደ ኢትዮጵያ ያመጣው የአስተዳደር ሥርዓት ነው፡፡ ሲያመጣው ግን ‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ› እያለ አብዮትም ዴሞክራሲም ያልሆነ አፋኝ ሥርዓት ነው›› ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ፡፡

ኢህአዴግ የተከተለው የፌዴራሊዝም ሥርዓት የሕዝቦችን ጥያቄ የሚመልስ ቢመስልም ‹‹የከፋፍለህ ግዛ የሞግዚት አስተዳደር ነው፡፡ ፌዴራሊዝም አለ ከተባለም ሕዝቦችን የጨቆነ፣ የሆነ ቡድንን የጠቀመ የውሸት ፌዴራሊዝም ነው፡፡ ፌዴራሊዝም በባሕሪው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ነው፤ በኢትዮጵያ አሁን ያለው ግን እንደገና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ማዋቀር የሚጠይቅ የከፋፍለህ ግዛ ግዛት ነው›› ሲሉም ፕ.ር መረራ ተችተውታል፡፡
ወደ ቀደመው የጠቅላይ ግዛት አስተዳደር የመመለስ ሐሳብ ያላቸው ሰዎችም መኖራቸውን የገለጹት ፕ.ር መረራ ‹‹ይኼኛው ሐሳብ መልሶ ወደ እርስበርስ ግጭት እንዳያስገባን እሰጋለሁ፤ መፍትሔው ሕዝቦች በፈለጉት አካባቢ በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲተዳደሩ መፍቀድ ነው›› ብለዋል፡፡
‹‹የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የሶማሌ፣ የጋምቤላ …ነፃ አውጭ ድርጅቶች ባሉበት፤ የአማራ ነፃ አውጭ የሚመስሉ ድርጅቶች እየተፈጠሩ ባሉበት ሁኔታ ወደቀድሞው አስተዳደር ሥርዓት (ጠቅላይ ግዛት) ለመመለስ መሞከር ዋጋ ያስከፍለናል፡፡ መፍትሔው የተጀመረውን የፌዴራላዊ ሥርዓት በሕዝቦች ፈቃድ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.