ፍርድ ቤቱ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በአቶ አብዲ መሐመድ ላይ ተጨማሪ የ14 ቀን የምርምራ ጊዜ ፈቀደ

Source: https://fanabc.com/2018/09/%E1%8D%8D%E1%88%AD%E1%8B%B5-%E1%89%A4%E1%89%B1-%E1%89%A0%E1%88%B6%E1%88%9B%E1%88%8C-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%88%AD%E1%8B%95%E1%88%B0-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8B%B3%E1%8B%B5%E1%88%AD/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፍርድ ቤቱ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሐመድና ጨምሮ በሌሎች ተከሳሾች ላይ ተጨማሪ የ14 ቀን የምርምራ ጊዜ ፈቀደ።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት 19ኛ ተረኛ ምድብ ችሎት በአቶ አብዲ መሐመድና በሌሎች በተጠርጣሪዎች ላይ የቀረቡትን አቤቱታ በዛሬው ዕለት ሰምቷል።

በዚህ ወቅት ተከሳሾቹ በቤተሰብ እንደማይጠየቁ፣ ምግብና ህክምና በተገቢው መንገድ እያገኙ እንዳልሆነ በመግለፅ ቅሬታ አቅርበዋል።

በተጨማሪም መዝገቡ ሁሉንም ተከሳሾች በአንድ የያዘ በመሆኑ በኋላፊነት ደረጃቸው መለየት እንዳለባቸውና የዋስትና መብታቸው ሊከበር እንደሚገባ ፍርድ ቤቱ ጠይቀዋል።

የቀረቡት ጉዳዮችን በዝርዝር የተመለከተው ፍርድ ቤት ፖሊስ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደረግ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ከዚህ ባለፈ የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብት ስለማየሰጣቸው ይህን ጥያቄ ውድቅ በማድርግ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለመስከረም 18 ቀጠሮ ይዟል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.