ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋርን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ

ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋርን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሃመድና በቀለ ገርባን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ ከጳጉሜን 2 እስከ ጳጉሜን 5 2012 ዓ.ም የተሰሙ የምስክር ቃል ተገልብጦ ወስዶ እስከ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም ክስ አንዲመሰርት ነው ብይን የሰጠው።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ሌሎች ከ11ኛ እስከ 14ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ደግሞ በ5 ቀን ውስጥ ክስ እንዲመሰርትባቸውም ትእዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ በዛሬ ውሎው ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ትእዛዝ ሳይሰጥ፤ ተጠርጣሪዎቹ በማረፊያ ቤት አንዲቆዩ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 93 መሰረት ትእዛዝ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋርን ጨምሮ እስከ 10ኛ ተራ ቁጥር ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ እስከ መስከረም 8 2013 ዓ.ም ክስ እንዲመሰርት ብይን ሰጠ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply