ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ላይ የተከፈተው መዝገብ ላይ ለመበየን ቀጠሮ ሰጠ አሥራት:_ መስከረም 6/2013 ዓ/ም በዋስትና እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኋላ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች በድጋሜ ታ…

ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ላይ የተከፈተው መዝገብ ላይ ለመበየን ቀጠሮ ሰጠ አሥራት:_ መስከረም 6/2013 ዓ/ም በዋስትና እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኋላ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች በድጋሜ ታ…

ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ላይ የተከፈተው መዝገብ ላይ ለመበየን ቀጠሮ ሰጠ አሥራት:_ መስከረም 6/2013 ዓ/ም በዋስትና እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኋላ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች በድጋሜ ታስረው ከሀጫሉ ግድያ በኋላ አመፅ አስነስተዋል በሚል ሌላ የምርመራ መዝገብ የተከፈተባቸው በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ለመስከረም 7/2013 ዓ/ም ለብይን ተቀጠሩ። ከሕዳር 12/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአሥራት ሚዲያ ላይ በተሰሩ ዘገባዎችና ፕሮግራሞች ምክንያት ኦሮሚያ ውስጥ አመፅ ተነስቶ በሰው ሕይወት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ደርሷል በሚል ተጠርጥረዋል ተብለው በቀጠሮ ከተመላለሱ በኋላ የዋስትና መብታቸው ሲከበር፣ ከእስር ቤት እንደወጡ እንደገና መታሰራቸው ይታወሳል። የአሥራት ጋዜጠኞች በድጋሜ የተከፈተባቸውን መዝገብ ከቀደመው ጉዳይ የተለየ አይደለም ብለው በመከራከራቸው ፍርድ ቤቱ የፖሊስና የፍርድ ቤቱን መዝገብ መርምሮ በድጋሜ የተከፈተባቸው መዝገብ ከቀደመው የተለየ ስለመሆን አለመሆኑ ለመበየን ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ ነበር። የቀደሙት የፖሊስና የፍርድ ቤት መዝገቦች ከቀጠሮው ቀደም ብለው በድጋሜ ከተከፈተባቸው መዝገብ ጋር እንዲያያዙ አራዳ መጀመርያ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ መዝገቦቹን ያያያዘው ዛሬ ጠዋት መሆኑን ተናግሯል። በዚህም ምክንያት ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት እንዳልቻለ ተገልፆአል። ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ሌላ መዝገብ የተከፈተባቸው ባለፈው ዋስትና ባገኙበት ተመሳሳይ ጉዳይ ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን ለመበየን ለመስከረም 7/2013 ዓ/ም ከሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply