ፒኮክ እና አንበሳ የማህበራዊ ሚዲያው የሰሞኑ አጀንዳ ሆነዋል – ሲሳይ አጌና

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/104002

በዕርግጥ ቤተመንግስት ላይ የነበረ አንበሳ አንስቶ በፒኮክ መቀየር ለምን አስፈለገ? የሚለውን ጥያቄ ከመጠየቅ በፊት የፒኮክ ምስል የት ተሰቀለ የሚለውን ምላሽ ማግኘት አስፈላጊ ነው ።በዚህም በኢዩቤልዩም ሆነ በአጼ ምኒሊክ ቤተመንግስት ላይ የተጨመረም ሆነ የተቀነሰ ወይንም የተለውጠ ነገር እንደሌለ ብረዳም ግራ ያልገባኝ ግራ በተጋባ መድረክ ውስጥ የሚንሸራሸር ሃሳብ በመሆኑ ነው። የደርግ ጉባኤ አዳራሽ በ1977 እስኪሰራ ድረስ ባዶ […]

The post ፒኮክ እና አንበሳ የማህበራዊ ሚዲያው የሰሞኑ አጀንዳ ሆነዋል – ሲሳይ አጌና appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

One thought on “ፒኮክ እና አንበሳ የማህበራዊ ሚዲያው የሰሞኑ አጀንዳ ሆነዋል – ሲሳይ አጌና

 1. ጉድ ነሽ የሽንኮበር ቅጠል!!
  ፻ ዓለቃ ሲሳይ አጌና “ላልነበረው አንበሳ መሟገት ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? በማስረጃ እንነጋገር ካልንም ከምናየውና ጨብጠን ከምንመነዝረው ዕውነታ የምንረዳው ጫጫታ ከሚያሰሙት በላይ የለውጡ መሪዎች ኢትዮጵያዊነታቸውን በተግባር እያስመሰከሩ መሆኑን ነው።ይህ ማለት መንግስት ላይ ጥያቄ የለንም ማለትም አይደለም ።ነገር ግን የፈረሰ ሃገር በመጠገን ላይ ያለ ቡድን ላይ ከአፍራሾች ሕወሃቶች ጋር ተደምሮ ሥልጣን ላይ ያለውን ቡድን ማስጨነቅ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚደረግ ትብብር ነው።በቅንነት በውዥንብሩ ውስጥ ሆነው ለሚጠይቁ ግን ፒኮክ ለሃገራችንም ለርዕሰ መዲናችንም እንግዳ እንዳልሆነች ማስታወሱ ተገቢ ነው። ፒኮክ ካፌ እና ፒኮክ መናፈሻ አዲስ አበባ ላይ ጎልተው የሚጠቀሱ የመዝናኛ ስፍራዎች የነበሩት ዛሬ ወይንም ትናንት ሳይሆን ከጥንት ከንጉሱ ግዜ ጀምሮ ነው።ገዳዮቹና አፋኞቹ እንዲሁም መልዕክተኞቻቸውን ጭምር ዛሬ በነጻነት የሚፏልሉበት ነጻነት በነጻ አልመጣምና።”
  ሊ/ጠበብት ጌታቸው ኅይሌ
  “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ከዘመናት ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት አርማ የነበረውን አንበሳን የጥላቻ ቃል አወረዱበት በሕዝብ ቈጠራ ኩሻውያን ኦሮሞዎች ስለሚበዙ፥ የተጫነባቸው የሴማውያን ባሕል ተወግዶ፥ ገለልተኛ የሆነ ሕዝብን በሚወክል ምልክት ለማምጣት ነው የሚሉ አሉ። አንዳንዶች ደግሞ ጣዎስ ባለብዙ ቀለም ላባ ስላላት ባለ ብዙ ነገዶችና ጎሳዎችን ስለምትወክል ነው ይላሉ። በአንድ ሰው ሥራ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ የአንድምታ ባህላችንን አዥጎደጐድንበት። የተለመደና የተወደደን የሕዝብ ባህል ለማስጠበቅ ሕግ ባይወጣም፥ አዲስ መሪ በመጣ ቍጥር የሕዝብን ባህል እሱን በሚያስደስተው ባህል የመለወጥ መብት የለውም። አንበሳን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋራ አይቶ ከመግፋት ይልቅ፥ ጎልማማ፥ ኩሩ፥ ምሉአ-ግርማ ኢትዮጵያዊ ፍጡር መሆኑን ለማየት የሚከለክለን ምክንያት አይኖርም።ዓለም ያወገዘውን የጎሰኝነት ፖለቲካን በማድረቅ ፈንታ የባሰውን እንዲያለመልም ውሐ ያጠጡታል ማለት ነው። ሌላውን ባይሰሙ፥ ለምን ያሁኖቹን የሱማሌ “ክልል” መሪዎችን ትምህርት እንደማይቀበሉ ግልጽ አይደለም። ጥረታችን የጎሳ አባላት በሚያኮራ በጉብዝናቸው እንጂ በጎሳ ማንነታቸው እንዲጠቀሙ መሆን የለበትም። “አማራ፥ ትግሬ፥ ኦሮሞ፥ ጉሙዝ፥ ወላይታ፥ ጉራጌ፥ ወዘተ. ስለሆንኩ ተራ ይድረሰኝ” ማለት ክብር-አልባ ልፍስፍስነተን መቀበል ነው።”
  *************
  ጠ/ሚኒስትሩ ፲፯ የደሃ ገበሬ ወጣት ልጃገርዶች ከመንገድ ላይ መታገትና መሰወር የሚበልጥባቸው፡ የመንገድ ዳር ፳ የፈካ የሸክላ ላይ አበባ መጥፋት ነው።የዱር እንስሣትና አበባ በኢትዮጵያ የቸገረ ይመስል ሌት ተቀን አበባ ውሃ አጠጡ ላይ መጠመዳቸው የከተማ አስተዳደሩ ምን ይሰራል? የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ደንና አራዊት ጥብቃ ምን ይሰራል? ለምን የግብና ሚ/ር ሆነው አምሮታቸውን እየተወጡ ” መክሊቴ መለመን ነው ከሚሉ” ይህን ሁሉ ሥራ አጥ ይዘው በመስኖ አርሰው ሀገር አይለውጡም? ቤተመንግስትን መንፈሻ (ፓርክ) ለማድረግ መራወጥ ቀጥሎ ደሞ የራቁት መጨፈሪያ (ዲስኮ) መታሻ ቤት፡ ይሰራ የሚል መካሪ ላለመምጣቱ ምን ዋስትና አለ? ጠ/ሚ አብዮት የአምስት ዓመት የኮንትራት (ጊዜያዊ) ተቀጣሪ እንጂ (ለዚያውም ካላቸው) የዕድሜ ልክ አልጋ ወራሽ ለመሆናቸው የታየላቸው ራዕይ አደገኛ ነው፡ የማያናንቁት የማይሰድቡት የማያጥላሉት ነገርና ሰው የለም፡ ጭራሽ ከጠቅላይ ሚ/ር ..ፕሬዘዳንት መሆን አልፎም ወታደራዊ መንግስት እንደሆኑም እያመለጣቸው ይሁን ሆን ብለው ማወጅን ይዘዋል፡ ይህ ሁሉ ውዥንብር ንቅለ ተከላ ወይንስ ገፅታ ግንባታ??
  ** ፕኮክ ካፌና ፒኮክ መናፈሻ ድሮም በንጉሱ ግዜ ነበር ማለት ካሊፎርኒያ ባር የሚባል አለ ማለት ካሊፎርኒያ ድሮ የእኛ ነበር ማለት ይሆን? ኦባማ ጠጅ ቤትም አለ አይደል? ይቺ ጎስቋላና ድሃ ሀገር ከጭቁን ሕዝቧ ጋር ወፍ መትከል ነው ስንዴ ዘርቶ ዳቦ ማምረት ቅድሚያ የሚሰጠው? ግን እንኝህ ብሔር ብሔረሰቦች እና (ሕዝቦች) መሳቂያ መሳለቂያ መሆን ማንም እየተነሳ በማንነታቸው በቀለማቸው አለባበስና ጭፈራቸው ሁሉ የሚቀለደው ለምን ይሆን? “ገዳዮችና አፋኞች (መልዕክተኞች)” ሲወገዙ እነኝህ የለውጥ ኅይል ሀገር አዳኝ ሰዎች እንዴት ነው እንዲህ ከደሙ ንጹህ ቅዱሳን ሆነው ንፋስ አይንካቸው የሚባሉት? ከጆሮ ጠቢነትና አደራ የተሰጠውን የሀገርን (የመንግስትን) ሚስጥር አውጥቶ ለባላንጣ ከመስጠት ሌላ የሀገር ክሕደትና ወንጀል ይኖር ይሆን? ይህ የጭብጨባ ሞቅታ ለታላቁ መሪም አልበጀ!! ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱም ተንሸራታች ነችና እየተስተዋለ!! ተረጋጋ በለው !!

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.