ፓርላማው ነገ የሚኒስትሮችን ሹመት ያፀድቃል

Source: https://fanabc.com/2019/04/%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%88%8B%E1%88%9B%E1%8B%8D-%E1%8A%90%E1%8C%88-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AE%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%88%B9%E1%88%98%E1%89%B5-%E1%8B%AB%E1%8D%80%E1%8B%B5/

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ የሚኒስትሮችን ሹመት ያፀድቃል ተበሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 34ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል።

በስብሰባውም የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ የሚያፀድቅ መሆኑን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም የምክር ቤቱን ውሎ በቴሌቪዥንና ኦን ላይን በቀጥታ የሚያስተላልፍ ስለሆነ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.