ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ሞት ሀዘናቸውን ገለፁ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/75242

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በሀዘን መግለጫቸው፥ “ክቡር የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየትን የሰማሁት በከፍተኛ ሃዘን ነው” ሲሉ ገልፀዋል።
“ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ኢትዮጵያን ከወጣትነት ዘመናቸው ጀምሮ በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት ያገለገሉና በአስቸጋሪ ውጣ ውረዶች ውስጥ በመገኘት ለሃገራቸው ያላቸውን ክብር በተግባር ያሳዩ ታላቅ ባለውለታ ናቸውም” ብለዋል።
ለ12 አመታት በፕሬዚዳንትነት ካገለገሉበት ከፍተኛ ሀገራዊ ሃላፊነት በተጨማሪ በየጊዜው እየተመናመነ የመጣውን የደን ሽፋን መልሶ እንዲያገግም ግንባር ቀደም የአረንጓዴ ልማት አርበኛ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽዎ አድርገዋል።
ጧሪና ደጋፊ ያጡ ወገኖችን ትኩረት እንዲያገኙ ሲያደርጉት የነበረው ጥረትም ሁሌም በመልካም ተግባራቸው እንድናስታውሳቸው የሚያደርግ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፦ “የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን በኢትዮጵያ ህዝብና በራሴ ስም እየገለጽኩ፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ” ማለታቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.