ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መልቀቂያ ማስገባታቸው እየተነገረ ነው

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81329

ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ዛሬ ማምሻውን የሥራ መልቀቂያ አስገብተዋል:: ከመንግስት ወይም ከፕሬዚዳንቱ በኩል የተሰጠ ማረጋገጫ ባይኖርም ከአንድ ወር በፊትዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በየ ዓመቱ ለህዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት ተፅፎ ተሰጥቷቸው ለሚያነቡት ጽሁፍ በተቻለ መጠን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ተደርጎ እንዲዘጋጅላቸው ማስጠንቀቀቂያ መስጠታቸው መዘገቡ አይዘነጋም:: ሌላኛው የኦህዴድ ከፍተኛ […]

Share this post

One thought on “ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መልቀቂያ ማስገባታቸው እየተነገረ ነው

 1. “ይህ እውነት ከሆነ እጅግ በጣም ጥሩና ተገቢ እርምጃ ነው!። በኢትዮጵያ በፕረዜዳንትነት ደርጃ የተቀመጡት ሁሉ በጭራሽ/በፍጹም ሥራና ኅላፊነታቸውን አላወቁትም ወይም እንዲሁ ለነበር(ሩ) የተጎለቱ ናቸው። በፕሬዘዳንትነት ማዕረግ የውጭ ንግድ አፈላላጊ በዓለም ልዩና ብቸኛ ያለው በህወሓት/ኢህአዴግ ሥራዓት ብቻ ነው።
  *ከቱርክ አምባሳደርነት ማዕረግ በተሾመ ማግስት ፓርላማ ያልሰራና ያልነበረበትን እሪፖርት አንባቢ ፕሬዘዳንት..(!?)
  *በሕዝብ ተቃወሞ የኢንቨስተር ንብረት ሲወድም ዓመድ ጎብኝቶ በማግስቱ ጥሊያን ኢንቨስተር አፈላላጊ…
  *ሀገሪቱ በአስቸኳይ አዋጅ ተጠርንፋ…በመደበኛ አስተዳደር መመራት አቅቷት በወቶአደር ስትመራ፡ ለጋራ አብሮ መኖር፡ ለሕዝብ ሰላምና ደህንነት ያለውን ሙሉ ሥልጣን ተጠቅሞ ፓርላማውን/ሚኒስትሮች ም/ቤት… ገዢ/አውራው/ነጻአውጭውን መንግስት፡ ከነጻ ወጭው ሕዝብ ምሁርና መከላከያ ጋር አብሮ ያልመከረ ፐሬዘዳንት፡
  * ሀገር በርሃብና በተቃውሞ ሲናጥ፡ የሀገር ማንነት(የጋራ እሴት ሲጠፋ) በሚሊየን የሚቆጠር የሕዝብ ገንዘብ የፈሰሰበት ፓላስ/የክብር የግል ቤት ግንባታ ላይ ተጠምዶ ነበር። ሥራው አልገባወም ወይ ግራ ተጋብቷል አሁን እቤቱ ገብቷል። በቋንቋና ነገድ የክልል ዜግነት(ግጦሽ) ሜንጫ ካማዘዘ፡ፌደራሊዝሙ እንኳን አብሮ ሊያኖር ኳስ አብሮ ካላጫወተ መጪው ዘመን ከፍታ ሳይሆን ሀገር ከበለጠ ውርደትና የትውልድ ቅሌት፡ የእርስ በርስ መተላለቅ ከመከተሉ በፊት…በግልጽ ወታደራዊ ሥርዓት ጠቅልሎ ቢያስተዳድረው አሁን ትውልድ ከገባበት አሳፋሪና አስነዋሪ ደርጃ የተሻለ እንደሆነ አምኖበት ስለሆነ ነው። ድሮስ የቻይና ትምህርትና ዕቃ ባትሉኝ!
  ህወሓት/ኢህአዴግ ደጋፊ/በተደጋፊው ጨብጫቦ ደንቁሮ እንጂ በተቃዋሚው/ተቋቋሚው ምንም አይሆንም ብለናል።

  Reply

Post Comment