ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ ከ250 በላይ የሚሆኑ የመስተዳድሩን ልዑካን መርተው ባህርዳር እንደሚሄዱ ተነገረ።

Source: http://www.mereja.com/amharic/554306

“ከዚህ በፊት በደም ተሳስረናል፣ ወደፊትም ይቀጥላል! በሚል መሪ ሃሳብ የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ ከ250 በላይ የሚሆኑ የመስተዳድሩን ልዑካን መርተው ባህርዳር እንደሚሄዱ ተነገረ።


ከኦሮሚያ አባገዳዎች፣ ከክልሉ ሽማግሌዎች፣ ከወጣቶችና ከተለያዪ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ልዑካንን በመምራት በመጪው ቅዳሜ ጥቅምት 25/2010 በባህርዳር በመገኘት በአይነቱ ልዪ የሆነ ኮንፍረንስ እንደሚያካሂዱ ተዘግቧል።
ባለፈው መስከረም ወር ከ200 በላይ የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች “ጣና ኬኛ” በማለት፣ በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ ወደ አማራ ክልል መምጣታቸውና፣ በክልሉ የሚገኙ ሌሎች ታሪካዊ ቦታዎችን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
“ከዚህ በፊት በደም ተሳስረናል፣ ወደፊትም ይቀጥላል!”

Share this post

One thought on “ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ ከ250 በላይ የሚሆኑ የመስተዳድሩን ልዑካን መርተው ባህርዳር እንደሚሄዱ ተነገረ።

 1. *** የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የልዑካን ቡድኑ ባሕርዳር ይሄዳሉ? ከዚያስ መቼም ብአዴን ውስጥ አማራ አያገኙም የህወሓት ሰፋሪ የአማራ ዕድገት አቀጫጮችን እንጂ…. ነገሩ ባልከፋ አማራ የሚደራደርለት ከእውነተኛ ኦሮሞ ጋር አንድ የሚያደርገው ሰው ብአዴን ውስጥ ሰው አለን?
  ****
  ይህ ቀደም ብሎ የጠላትነት ሐውልት በተልዕኮ ከመትከል፡ የፍቅር ድልድይ፡ የይቅር ባይ መሰላል፡ ተገንብቶ ቢሆን ወገኖቻችን ፵፬ ዓመት ጥላቻን ዘርተው ድህነትን..ክልልን አጥረው የበይ ተመልካች…ቋንቋን የልዩነት ሰንደቅ አድርገው አትድረሱብን ልዩ ነን ብለው ተለይተው አንዱ እንዱስትሪ መር ክልል ሲሆን፡ ሌላው መሬት አልባ ተመጽዋች ሆኖ ትውልዱ መክኖ ባልባከነ ነበር። ጥላቻን፡ዘረኝነት፡ጽንፈኝነት፡የየዋህ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጸየፈው ምግባር ነበር፡ ዕድሜያቸው ይጠርና ህወሓት ባንዳ/የሹምባሽ ልጅ የልጅ ልጆች እና የሚሽነሪ ፋፋና የወተት ዱቄት ናላቸው የዞረ ከሁሉም ጎራ፡ ሀገራዊ ወርቃማ የአብሮነት ኑሮ፡ ባሕልና ወጋችን እንዲጠፋ አደረጉ ትውልዱ ጠፋ! ..በረከቱን ሰላሙን አጣን! ወደድንም ጠላንም፡ ከነጭ ከግዛት ቅኝ ተገዥነት ነጻ ሆነን ተወልደን፡ በነፃነት የኖርነውን ያህል፡ የነጭ የሸቀጥ ማራገፊያ ሆነን የኢኮኖሚ ባርያ ላለመሆን ዋስትናው አንድነት፤ እኩልነት፤ አብሮ ሠርቶ አብሮ ማደግ፤ እንጂ ንብረት አውድሞ አመድ መታቀፍ ድል አደለም።
  ..ይልቁንም እያንዳንዱና ሁሉም የውስጡን ስንኩል አስተሳሰብ፡ አረመኔያዊ ተግባር አፍላቂ፡ የትውልድና የሀገር ነቀርሳ፡ አድርባይ! ዓረም እየነቀለ አካባቢውን ካላፀዳ ሀገረ ኢትዮጵያና ሕዝቧ ሠላምም፡ ጤናማም፡ አትሆንም!። …መጪው ዘመን የከፍታ ዝላይ ሳይሆን የአንድነት ብቻ ሳይሆን የውሕደት ይሆናል..****

  ግድየለም ግድየለም ፍቅር ፍቅር ያለ የማይሆነው የለም አለ ከያኒው…

  ዓረም ነቀላ በጣና ! የውይይት መድረከ ባህር ዳር! _________ ! የፍቅር ቀጠሮ በጎንደር!

  ›We can not believe how shortsighted the leaders of ANDM and TPLF were to allow the escalation of last year’s mayhem in Amhara region! For one thing they allowed anti peace elements to own the agenda and worst they allowed extremists to put wedge between the two people who are the two faces of the same coin. The result is what we see today – Ethiopia is being ruined down by hooligans in Oromia! Today Jawar and company are more informed about events unfolding within EPRDF than loyal supporters! Jawar is being fed daily update while supporters are fighting gag-order to inform the public. All of this has been the end result of the fracture between TPLF and ANDM two pillar organizations within EPRDF. This was not what the martyrs were promised! Sad! (አይጋ ፎረም)

  Reply

Post Comment