ፖለቲካ የወለደው ዘርንና ቋንቋን መሰረት ያደረገው አደረጃጀት እንደ ሀገርና እንደ ህዝብ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን ፈጥሮብናል ሲሉ የመኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አብርሀም ጌጡ ተናገሩ።…

ፖለቲካ የወለደው ዘርንና ቋንቋን መሰረት ያደረገው አደረጃጀት እንደ ሀገርና እንደ ህዝብ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን ፈጥሮብናል ሲሉ የመኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አብርሀም ጌጡ ተናገሩ።…

ፖለቲካ የወለደው ዘርንና ቋንቋን መሰረት ያደረገው አደረጃጀት እንደ ሀገርና እንደ ህዝብ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን ፈጥሮብናል ሲሉ የመኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አብርሀም ጌጡ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል “እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ያልተሻገርናቸው ፈተናዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን” በተመለከተ ፓርቲያዊ አቋማቸውንና ምሁራዊ እይታቸውን እንዲያጋሩን በሚል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ አብርሀም ጌጡን አነጋግሯል። አቶ አብርሀም ሲቀጥሉ ፖለቲካ የወለደው ዘርንና ቋንቋን መሰረት ያደረገው አደረጃጀት ፈርጀ ብዙ ችግር ፈጥሮብናል ሲሉ ተደምጠዋል። “እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ያልተሻገርናቸው ፈተናዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን”ለማመላከት ባለመው ውይይት ላይ ሀሳባቸውን ያገሩን አቶ አብርሀም አሁን ላይ ለደረስንበት ሀገራዊ ምስቅልቅል ቋንቋንና ዘርን መሰረት አድርጎ የተዋቀረው ጤነኝነት የጎደለው ፖለቲካዊ አደረጃጀት ነው ብለዋል። ወደ ኋላ ተመልሰው ታሪክን የነቀሱት አቶ አብርሀም በ1880ዎቹ በበርሊን ኮንፈረንስ ላይ በሀያላን አገሮች የተወሰነው አፍሪካን ለመቀራመት ያለመው ምደባና ዘመቻን ተከትሎ ኢትዮጵያ ለጣሊያን ተመድባ እንደነበር አውስተዋል። ጣሊያንም አንድ አይሉ ሁለት ጊዜ ከባድና ዘመናዊ መሳሪያ በመታጠቅ ኢትዮጵያን ለመውረር የሞከረች ቢሆንም ቀደምት ጀግኖቻችን የመሪነት ጥበብና አንድነትን ተጠቅመው በኋላቀር መሳሪያ አሳፍረውና ድባቅ መተው በመመለስ የጥቁር አፍሪካዊያን ኩራት የሆነች ነጻ ሀገር አስረክበውናል ነው ያሉት። ይህን ተከትሎም ነጮችና አረቦች ለማንም የማትበገረ ሀገረ እግዚአብሄር የሆነች ገናና ታሪክ ያላት ሀገርን ለማንበርከክ እንደማይችሉ መረዳታቸውን ተከትሎ የውስጥ ተልዕኮ ፈጻሚ የሆኑ የራሳችንን ሰዎች ማደራጀት እንደ አይነተኛ አማራጭ እስትራቴጅ አድርገው እንደወሰዱ ጠቅሰዋል። በጦርነት ድባቅ የተመቱበትና አላማቸው እንዳይሳካ ያደረጉ፣ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ የአብሮነት ስሜትና የሰብሳቢነት ሚና አላቸው ያሏቸውን አማራንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቤተ ክርስቲያን ከተቻለ ማጥፋት ካልሆነም መበታተንና ማዳከምን መርጠው የገበቡት ትግል ነው ብለዋል። በዚህም ትህነግንና መሰሎቹን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አደራጅተው በርካታ ዜጎች ከጎጣቸው፣ከመንደራቸው፣ከወንዛቸው፣ከብሄራቸው አልፈው ለማየት እንዳይችሉ በዘር እና በቋንቋ ሆንብለው እንዲጠመዱ አድርገዋል ሲሉም አክለዋል። ይህን የመለያየት፣የሀሰትና የጥላቻ ትርክት ባለፉት በርካታ ዓመታት የሀገሪቱን ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ሚዲያና ሌሎች ሀብቶችን በብቸኝነት በተቆጣጠረው ህወሀት ሲሰበክና ሲዘራ መቆየቱ የአስተሳሰብ ብክለትና ዝንፈት አምጥቷል፤ አሁን እያጨድን ያለንው እሱን ነው፤ይህም አንዱ ትልቅ ሀገራዊ ፈተና ነው ብለዋል። ከአባይ የውሀ ፖለቲካ ጋር በተያያዘም ከውጭ ነጮች፣ግብፅ፣ሱዳንና ሌሎች አረቦችም እንዲሁም ከሀገር ውስጥም ተልዕኮ ፈጻሚዎቻቸው አርፈው የማይቀመጡ መሆናቸው ሌላኛው ያልተሻገርነው ፈተና ስለመሆኑም ጠቅሰዋል። ምንም እንኳ መኢአድ ከተለያዩ መሰረታዊ ምክንያቶች በመጥቀስ ለውጥ አለ ብሎ ባያምንም ዛሬም ቢሆን የለውጥ ኃይል ነኝ የሚለው ቡድን ከነበርነባቸው ተረኛና ጎታች መንደርተኛ አስተሳሰቦች አለመፋታቱና መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የፍላጎት እጦት ማሳየቱ ሌላኛው ፈተና ስለመሆኑ ተናግረዋል። በመሆኑም ዛሬም ከትናንቱ በባሰ መልኩ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመ ነው ያሉት አቶ አብርሀም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎችም ንፁሀን በታጠቁ አካላትና በመዋቅሩ በተሰገሰጉ አካላት እኩይ ተሳትፎ ጭምር ውድ ህይወታቸውን ማጣት ጨምሮ ለአያሌ መከራዎች እየተዳረጉ ይገኛሉ፤ በዋናነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና በአማኞች ላይም ጥቃቱ በዛው ልክ ቀጥሏል ብለዋል። ዘርፈ ብዙ ፈተናዎችን ለመሻገርም መፍትሄው በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ ለመነጋገር መዘጋጀት ነው ያሉት አቶ አብርሀም ለዚህም መንግስት የአንበሳውን ድርሻ መውሰድ ያለበት ቢሆንም የተለያዩ የፖለቲካ ሀይሎች፣አደረጃጀቶችና ህዝብ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ አሳስበዋል። ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ከፓርቲው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ከአቶ አብርሀም ጌጡ ጋር በ3 ክፍል ያደረግነውን ውይይት የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply