ፖለቲካ የጠፋቸው ፖለቲከኞች (ሃይሉ አባይ ተገኝ)

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/42594

በጣም ይገርማል። በጣም ያሳፍራል። አጅጉን ያሳዝናል።

በዚህ ጊዜ ጭራሹን አንዳንድ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች አንኳንስ ህዝብን የሚያክል ትልቅ ነገር የራሣቸውን ስሜት መግራትና መምራት ተስኗቸዋል። ፖለቲካዊ ታሪክንና ስልትን ግብ፤ ስትራቴጂን ጊዜያዊ ስልት አድርገውታል። በጣም ይገርማል።

የሰሞኑ የፖለቲካ መድረክ ተዕይንት የሚያሣየን ፖለቲከኞቻችን በጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ ድስት ላይ ተጥደው ሲንተከተኩ ነው። አቶ ለማ፣አቶ አብይ ወዘተ. ጠቅላይ ሚኒስትር ይሁኑልን አያሉ ወያኔን በመጎትጎት ይሞነጫጭራሉ። ከአነዚህ ግለሰቦች መሃል አንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሆን ችግር የለውም። ነገር ግን ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን መመረጥ ያለበት በፖለቲከኞችና በደጋፊዎቻቸው ሳይሆን በዲሞክራሲያዊ አግባብ በህዝብ ብቻ ነው። ይህን ዲሞክራሲያዊ መርህ መናድ ኢ-ዲሞክራሲያዊነት ነው። አጣብቂኙ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ወይም ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲያደርጋቸው የሚጠይቁት ህዝባዊ ስርዓትን ሣይሆን ህወሃትን ነው። በጣም ያሳፍራል። የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን፣የሕግ የበላይነትንና የዜጎችን በነፃነት ሃሳብን የመግለፅ መብቶችን ጨፍልቆ ጭራሹን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጠፈራቸውን የሽፍታ መንግስት የኛ አንዳንድ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች የሚፈልጉትን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሾምላቸው ታቦት ይዘው ሲማፀኑ ይስተዋላል። ጭራሹን ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትር ማከናወን ያለበትን “ሰባቱን ትዕዛዛት” ሲዘረዝሩ አስተውለናል። ልጆቿ ግራ የሚያጋቧትና ሃገርና ፖለቲካው የጠፋባቸው ፖለቲከኞቻችን። አረ ለመሆኑ ህወሃት ስልጣን ለቀቀ እንዴ?

ወታደራዊና የደህንነት መቃቅሩን፣ ፖለቲካዊ ስልጣንንና አኮኖሚያዊ የበላይነቱን ለራሱና በራሱ ቁጥጥር ስር አድርጎ የያዘን አፓርታይዳዊ ወያኔን የስልጣን ዘመኑ እስካላከተመ በስሩ ለሚቆጣጠራቸው መንግስታዊ መዋቅሮች ፍፁም ታማኝነት /pledge allegiance/ ለሌለው ወይም ለማይኖረውና ፖለቲከኞቻችን ለመረጡት ወይም ለሚመርጡት ግለሰብን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ከሾመ ስልጣኑን በፈቃዱ ለመልቀቅ ወስኗል ማለት ነው። ይህ ካደረገም ህወሃት አምባገነን ሣይሆን ዲሞክራት ነበር ማለት ነው። በህወሃት መዳፍ ስር ያሉት መንግስታዊ መዋቅሮች ሳይነኩ እንኳን እነ አቶ ላማ ክርስቶስ፣ነብዩ መሃመድና ቡድሃ በጥምር በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቢሾሙ መሠረታዊ ለውጥ ሊያመጡ ቀርቶ አይሞክሩትም። ፖለቲከኞቻችን ፖለቲካ የዛሬ ታሪክ ሆኖ በህዝብ ተሳታፊነትና በነባራዊ ሁኔታዎች እንደሚወሰን ክፉኛ ዘንግተው “ታሪክ ይሰራሉ” የሚሉዋቸውን ግለሰቦች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲያጩ አየናቸው። አጅጉን ያሳዝናል። ፖለቲከኞቻችን እናገለግልሃለን የሚሉትን ህዝብ ወደጎን አድርገው ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ በማይታሰብበት የአፓርታይድ ስርዓት ውስጥ በህዝብ ስም ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሾሙልን ይታያል። ይህ ያሳፍራል። ከፊታችን የሚያቆሙልን ፖለቲካዊ አስተሳሰብና ስርዓት ይህ ከሆነ እንደገና ያሸማቅቃል።

ለእኔ ቅድመ ሁኔታዎቹና መፍትሄው የሚከተለው ይመስለኛል።

ሀ).ቅድመ መንግስታዊ ስልጣን ዝግጅት

 1. ፖለቲካዊ ፍጥጫ (political confrontation) ለማስወገድ ፖለቲካዊ ሰጥቶ መቀበልን መርህ ያደረገ መቻቻልና ድርድር (tolerance & compromise) በማድረግ ፖለቲካዊ ልዩነቶችንና አመለካከቶችን ማጥበብ
 1. ለፖለቲካ ልዩነቶች መፍቻ የህዝብን ውሳኔ መፍትሄ አድርጎ መቀበል
 2. ፖለቲካዊ አሳታፊነትን ማበረታታት
 3. ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በማክበር ሁሉንም አመለካከትና ሃይሎችን የሚያካትት አንድ ወጥ የሆነ ህብረት መፍጠር የመጀመሪያ እርምጃዎች ናቸው።

ለ). ድህረ መንግስታዊ ስልጣን ክንዋኔዎች

 1. በዲሞክራሲያዊ፣ በህግ የበላይነትና በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ላይ የተመረኮዘ፤በህዝብ ይሁንታና ድምፅ የሚተገበር የሽግግር ጊዜ ሠነድ ማዘጋጀት
 1. ሁሉንም የማሀበረሰብ ክፍሎችና ፖለቲካዊ ሃይሎችን ያካተተ፤የለውጥ ሂደቱን የሚያቀላጥፍ ተጠሪነቱ ለህዝብ የሆነ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት ማቋቋም
 1. ወያኔያዊ የአፈና መዋቅሮችን ማፈራረስ
 2. ስልጣንን በህዝብ ለሚመረጥ መንግስት ማስረከብ ጥቂቶቹ ናቸው።

ለነዚህ ተግባራዊነት በቅድሚያ የወያኔ መንግስት መወገድ ይኖርበታል። ፖለቲከኞቻችንም ለጥገና ለውጥ ሳይሆን ለመሰረታዊ የስርአት ለውጥ መምጣት ሃይላቸውን አቀናጅተውና በመርህ ላይ አተኩረው ካልሰሩ የወያኔ መንግስት በቀላሉ ይወድቃል ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል። የዚህ ቀደሙ የአምባገነኖች ታሪክ የሚዘክረው ስልጣንን ፈቅደው አለመልቀቃቸውን ብቻ ነው።

Share this post

One thought on “ፖለቲካ የጠፋቸው ፖለቲከኞች (ሃይሉ አባይ ተገኝ)

 1. When you talk of PM it is about transition
  Nobody talked Lemma Megersa becoming PM for life. As to me he is a far better person than any politician I know so far and endorse him to be PM for two terms. On the other hand the saying bringing Lemma to PM position is not beneficial is a very poor political mindset. The PM is a powerful position in Ethiopia. He is the army commander, he can demote and promote anyone in the government. Please do not try to brainwash Ethiopians with narrow outlook. I was surprised Esat doing the same mantra. If a PM has the desire to change the political landscape, he/she has immense power to do so.

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.