ፖሊስ ፍልዉሃ መስጊድ አካባቢ እያነፈነፈ ነው

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81494

(BBN) ባለፈው አርብ (ጁመአ) በ አዲስ አበባዉ የፍልውሃ መስጊድ የሰገዱ ምእምናን መስጊዱ አካባቢ ለየት ያለ የፖሊስ ስምሪት እንደነበር አሳዉቀዋል።

ወትሮም በአንዋርና በሰፈር በኒ መስጊዶች የሚሰፍሩት ፖሊሶች ወደ ፍልዉሃ በማምራት ለሰላት የሚገቡ ወጣቶችን አስቁመዉ ሲያናግሩ እንደነበር ታዉቋል።መስጊዱ ዉስጥ ቦታ ስለሚጠብ ምእምኑ ዉጪ መስገድ እንዲችል ወረቀት የሚሸጡ ህጻናትን ሳይቀር ፖሊሶች እያባረሩ ነበር የሚሉት ምእምናን፣ዉጪ አንጥፎ ለመስገድ እየተከለከልን ወደ ግቢ እንዲገባ ሲያስገድዱ ነበር በማለት ገልጸዋል።

የፖሊሶቹ ስምሪት እኛ ለማሸማቀቅ ቢሆንም፣ ይህንን የመሰለው ወከባ የማይበግረን፣ከመስጊዶቻችን መንግስት እጁን እንዲያወጣ የምንሻ ሰላማዊ ዜጎች በመሆናችን በዉስጣችን የሰረጸው የለዉጥ ፍላጎት የማይቀለበስ ነው ሲሉ ምእምናኑ ለቢቢኤን ገልጸዋል።

ነገ በአዲስ አበባም ይሁን በክልል (በክፈለ ሃገር) መስጊዶች በሚደረገው የጁመአ ሶላት ተመሳሳይ የሆነ የፖሊሶች ስምሪትና ወከባ ካላ አድምጮቻችንና ከወዲሁ አንባቢዎች መረጃን ቢልኩልን ለህዝብ የምናቀርብ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

Share this post

Post Comment