ከህወሓት ጋር ውህደት አስክሬን አቅፎ እንደ መተኛት‼

Source: https://mereja.com/amharic/v2/174910

ከህወሓት ጋር ውህደት አስክሬን አቅፎ እንደ መተኛት‼
ስለ ህወሓት የሆነ ነገር በተባለና በተፃፈ ቁጥር “በትግራይ ህዝብ ላይ የተቃጣ ጥቃትና መገለል ነው!” በማለት እሪሪሪ ያላሉ። ይሄን የሚሉት ደግሞ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የህወሓት አባላት እና በሀገር ውስጥ እስከ ውጪ የሚገኙ የድርጅቱ ደጋፊዎች ናቸው።
ስለ አንድ ማፊያ ቡድን በተናገርክ ቁጥር በስሙ የሚነግዱበትን ህዝብ ተሳደብክ ይሉሃል። በእርግጥ እነሱ እንዳሉት ተሳድበህ ቢሆን እንኳን ወልዶ ባሳደገ ህዝብ ከመነገድ አይብስም። እውነት ለመናገር ህወሓትን አምርረው የሚጠሉት ሰዎች ለትግራይ ህዝብ ከህወሓቶች አስር እጥፍ የሚበልጥ ፍቅርና ክብር ያላቸው ናቸው።
የትግራይን ህዝብ ምንም ያህል ብትጠላው የህወሓትን ያህል ጠላት አታፈራለትም። ይህ የማፊያ ቡድን ለትግራይ ህዝብ ያተረፈለት ነገር ቢኖር ጥላቻና ጠላት ነው። አሁንም ቢሆን ህወሓት በህዝብ ላይ ጦርነትና ዕልቂት እንዲመጣ እየፀለየ ነው። ህወሓት ወደ ስልጣን የመጣው የሃውዜንን ህዝብ አስጨፍጭፎ ነው።
የኤርትራን ጦር ያሸነፈው የኣይደር ህፃናትን አስጨፍጭፎ ነው። ባድመ ላይ 70ሺህ ወታደሮች የሞቱበትን የደም መሬት ለወራሪው ሃይል በነፃ ያስረከበ ከሃዲ ነው። በጎንደር፣ ቆቦና ወልዲያ የትግራይ ተወላጆች ላይ ብሔር ተኮር ጥቃት ተፈፅሟል እያለ የአዞ እምባ ሲያነባ የነበረው ራሱ ገድሎና አፈናቅሎ ነው። አሁን ላይ እያደረገ ያለው በተመሣሣይ መንገድ ህዝብን ጨፍጭፎና አስጨፍጭፎ ስልጣን መቆጣጠር ነው!

በእርግጥ ከህወሓት ጋር መደመር ከፋሽስት ኢጣሊያ ጋር አብሮ እንደመስራት ይቆጠራል። ከህወሓት ጋር ጥምረት ለመመስረት ጥረት የሚያደርጉ ወገኖች ሀገራቸውን ከከዱ ባንዳዎች አይለዩም። ከህወሓቶች የሚደርስበትን በደልና ጭቆና በመፍራት አንገትን ደፍቶ መኖር በጠላት ወረራ ግዜም

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.