1 ሺህ 494ኛው የመውሊድ በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/11/1-%E1%88%BA%E1%88%85-494%E1%8A%9B%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8B%8D%E1%88%8A%E1%8B%B5-%E1%89%A0%E1%8B%93%E1%88%8D-%E1%89%A0%E1%88%98%E1%88%8B-%E1%88%80%E1%8C%88%E1%88%AA%E1%89%B1-%E1%8A%A5%E1%8B%A8/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 494ኛው የነብዩ መሃመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በዛሬው ዕለት በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው።

በዓሉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እንድሪስ፥ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በመተሳሰብ፣ የተቸገሩ ወገኖቹን በመርዳት እና ሰላምና አንድነት በመፀለይ መሆን እንደሚገባው አሳስበዋል።

የመውሊድ በዓልን ህዝበ ሙስሊሙ ሲያከብር ሰላም እና አንድነትን የሚያጠናክርበት እና የነቢዩ መሃመድ አስተምህሮቶች የሚተገበርበት ሊሆን እንደሚገባም ነው የተገለፀው፡፡

የመውሊድ በዓልን የሙስሊሙ ማኅበረሰብ በመላ ሀገሪቱ የተለየዩ አካባቢዎች አንድ ላይ በመሰባሰብ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ነው እያከበረ የሚገኘው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.