(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010) በኒዮርክ ትላንት አንድ ግለሰብ የእቃ መጫኛ መኪናን በመጠቀም ባደረሰው ጥቃት ስምንት ሰዎች ሲሞቱ ከ10 በላይ ቆሰሉ። የሽብር ጥቃት ነው በተባለው በዚህ አደጋ ህይወታቸውን ካጡት መካከል ለጉብኝት የመጡ አምስት አርጀንቲናውያን ጓደኛሞች እንደሚገኙበት ታውቋል። ጥቃቱን የፈጸመው የ29 አመቱ ኡዝቤክስታናዊ…

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)በአስመራ ከተማ ለተቃውሞ የወጡ ተማሪዎች በፖሊስ ተኩስ መበተናቸው ተዘገበ። በከተማዋ የተሰማውን ተኩስ ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት ለዜጎቹ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ታውቋል። የተቃውሞው መነሻ የኮሚኒቲ ትምህርት ቤቶችን ወደ ሕዝብ ትምህርት ቤት ለመቀየር ከተያዘ ዕቅድ ጋር የተገናኘ መሆኑም ተመልክቷል። በተኩሱ የሞተም ሆነ…

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)ሰማያዊ ፓርቲና አረና ትግራይ ሰላማዊ ሰልፎች መጥራታቸው ተገለጸ። ሰማያዊ በአዲስ አበባ፣ አረና ደግሞ በመቀሌ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ የፊታችን እሁድና ቅዳሜ የሚካሄዱ ናቸው። የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታነህ ባልቻ ለኢሳት እንደገልጹት ‘’ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት” በሚል ርዕስ የተጠራው ሰልፍ…

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)በአዳማ እየተካሄደ ያለው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ በላይኛውና በታችኛው ካድሬ አጀንዳ አለመስማማት ተራዘመ። በጉባኤው የግል ስልክን ጨምሮ ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ እንዳይገባ ጥብቅ ፍተሻ ተደርጓል። እሁድ ጥቅምት 19/2010 በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ በአንድ ቀን ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረው የኦህዴድ ድርጅታዊ…

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 22/2010)በኢሉባቡር መቱ ከሳምንት በፊት በተነሳ ግጭት ለተፈናቀሉና በመጠለያ ጣቢያ ለሚኖሩ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ በተቋቋመ ኮሚቴ አማካኝነት የተሰበሰበ የእርዳታ ገንዘብ ከደህንነት መስሪያ ቤት በወጣ ቀጥተኛ ትዕዛዝ መታገዱ ተሰማ። ከ1500 በላይ ለሚሆኑት ለነዚህ ተፈናቃዮች የተሰበሰበው ገንዘብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 4…