አረና ትግራይ ቅዳሜ ዕለት በመቀሌ የጠራው ሰልፍ በፀጥታ ኃይሎች አማካኝነት የታወከ እንደነበር ገልፆ ነገር ግን በብሔር ላይ ያነጣጠር ግድያ ይቁም፣እኛ ኢትዮጵያውያን አንድ ነን፣ ሕወሓት የትግራይ ሕዝብን አይወክልም የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን የያዘ ሰልፍ መካሄዱን አስታውቋል።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 27/2010) በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት በአንድ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት 26 ሰዎች ሲሞቱ 20 ደግሞ ቆሰሉ። የሟቾቹ እድሜ ከ18 ወር ሕጻን እስከ 77 ባለው ክልል ውስጥ ነው በተባለው በዚህ ጥቃት 8 የአንድ ቤተሰብ አባላትም መገደላቸው ታውቋል። ጥቃቱን የፈጸመውም የ26…

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 27/2010)132 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ ናይሮቢ በፖሊስ መታሰራቸው ተነገረ። ኢትዮጵያውያኑ በሚኖሩበት መንደር ተከበው የታሰሩት በሕገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብታችኋል በሚል ነው። በዚሁ አይነት ተመሳሳይ ዘመቻ ሌሎች ተጨማሪ 67 ሰዎች በሌላ አካባቢ ናይሮቢ ውስጥ በጅምላ መታሰራቸው ታውቋል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ በኬንያ…

በኢትዮጵያ በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን በአለፈው ዓመት መጀመሪያ ላይ በተፈጠረው ብሄር ተኮር ግጭት ከ28 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ልዩ መግለጫ አስታወቀ፡፡

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 27/2010) ታዋቂው የእስልምና እምነት መምህር ኡስታዝ አብዱልመጂድ ሁሴን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በቴሌቪዥን በሚያቀርቡት የእልምና ትምህርቶች የሚታወቁት እኚህ መምህርና ሰባኪ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትላንት ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል። ዛሬ በአዲስ አበባ ኮልፌ የሙስሊሞች መካነ መቃብር በሺዎች…

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 27/2010)በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ በህወሀት መንግስት አማካኝነት ለማካለል በታቀደው የቅማንት አስተዳደር ጉዳይ ላይ የተጠራውን ስብሰባ ነዋሪው ረግጦ መውጣቱ ተገለጸ። ያለህዝበ ውሳኔና ፍቃድ በህወሀት መንግስት የተካለሉትን 42 ቀበሌዎች የሚያቅፈው የቅማንት ልዩ ዞን በሚል ለሚዋቀረው አዲሱ አስተዳደር በዋና ከተማነት በተመረጠችው…

ቅዳሜ ማታ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የሳዑዲ ልዑላንና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም አላሙዲ መሬት ላይ ተኝተው የሚያሳይ ፎቶ ዴይሊ ሜይል በድረገጹ ላይ ለቋል። “ቂሊንጦ” በሚሰኝ ሁኔታ “አገልግሎት” እየተሰጣቸው እንደሆነ ከዴይሊ ሜይል ዘገባ ለመረዳት ይቻላል። “ከሳዑዲ መንግሥት ምንጮች የተገኘ” በማለት ዴይሊ ሜይል…

ኢትዮጵያው ትውልድ ያላቸው አል-አሙዲ በኢትዮጵያ ቁጥር አንድ የግል ኢንቨስተር ሲሆኑ፤ በኢትዮጵያ የሚወክሏቸው የግል ጠበቃ መታሰር፤ አለመታሰራቸውን ሳያረጋግጡ፤ ዜናውን እንደማንኛውም ሰው እንደሰሙ እስከ ትናንት ጠዋት ድረስ በስልክ እንዳገኟቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ክፍለ ሃገር አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተኩስ ከፍቶ ሃይ ሥድስት ሰው ገድሎ ሌሎች ከሃያ በላይ ያቆሰለው የሃይ ስድስት ዓመት ዕድሜው ዴቪን ኪሊ ጥቃቱን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳው የቴክሳስ ባልሥልጣናት ክትትል ይዘዋል።

ባለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያ አስከፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ያስከተሉ በርካታ የብሔር ተኮር ጥቃቶችና ግጭቶች ተካሂደዋል። እነዚህ ብሔር ተኮር ጥቃቶችና ግጭቶች መንስዔዎች እንዲሁም ያደረሱትን ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ፣ ስነልቡናዊና ሞራላዊ ጉዳት በትክክል ለማወቅና ለመግለጽ በጣም ሰፊ፣ ጥልቅና ተከታታይ ጥናቶችና ትንተና እንደሚጠይቅ ግልጽ ነው።