(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010) በኦሮሚያ ክልል ያሉ አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በመከላከያ ሃይል እንዲጠበቁ መደረጉ ተሰማ። የፖሊስ ሃይሉን ገሸሽ ያደረገ ይህ ተግባር ምናልባትም አመጽ እያሰማ ያለውን ህዝብ በሃይል ለማፈን የተቀነባበረ ሴራ መኖሩን እንደሚያሳይ ምንጮች ገልጸዋል። በክልሉ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችም ግቢዎቻቸውን እየለቀቁ…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010) የፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀድሞ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ ማይክል ፍሌን ዛሬ በፍርድ ቤት ጥፋተኝነታቸውን አመኑ። ማይክል ፍሌን በፍርድ ቤት ቀርበው የሀገሪቱ የፌደራል ምርመራ ቢሮ/ኤፍ ቢ አይ/ ጉዳዩን በተመለከተ ባደረገላቸው ምርመራ መዋሸታቸውን አምነዋል። የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ…
ጋዜጠኛ ሳሙኤል ፈረንጅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010)  በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በጋዜጠኝነትና በስራ አስኪያጅነት ለረጅም አመታት ያገለገለው ጋዜጠኛ ሳሙኤል ፈረንጅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ሳሙኤል ፈረንጅ ከጋዜጠኝነቱ ሌላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ማገልገሉ ታውቋል። አቶ ሳሙኤል ፈረንጅ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በጋዜጠኝነትና…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 22/2010) የ104 ዓመት አዛውንት ሴት በእስር ቤት በድብደባ ተገደሉ። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ በሚገኝ እስር ቤት ባለፈው ረቡዕ የታሰሩት ወ/ሮ አምባሮ ሺክህ ዳይብ በደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸው አልፎ ዛሬ አስከሬናቸው ለቤተሰብ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል። የእሳቸው ልጅ የ83 ዓመቱ አዛውንት አሊ…
በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ትዕዛዝ ተላለፈ

(ኢሳት ዜና– ሕዳር 22/2010) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ ሰክረው በፈጠሩት ችግር ምክንያት ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ትዕዛዝ አስተላለፈ። ዲፕሎማቱ ተስፋኪሮስ ሃይሉ ገብረማርያም ባለፈው ቅዳሜ በስካር መንፈስ መኪና ሲያሽከረክሩ ካደረሱት ተደራራቢ የትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ሲያስቆማቸው…

“ስደት ይብቃ!” የስደትን አስከፊነትና በወገኖቻችን እየደረሰ ያለቀውን ሰቆቃ እንደ አዲስ እናየው ዘንድ በአረባዊቷ አፍሪካ ሀገረ በሊቢያ የሚፈጸመውን ግፍ እያየን ነው በታላቅ ክብርና ሞገስ የሚታወቀው ወገኔ ዛሬ ክብሩ ቀርቶ ለሽያጭ በደረሰ የግፍ ቀንበር ተጭኖበታል … ውርደት አንገታችን አስደፍቶናል፣ ከሰው ተራ አውጥቶናል!…

መቅደላ –  የዐኅኢአድ ልሣን የዐማራው ኅልውና መጠበቅ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው! ሁለት ሺ አሥር የትግሬ-ወያኔ ከፋፋይ አገዛዝ ማክተሚያው ወይስ እንዳለፉት ሁሉ ሞቶ መነሻው? ከመነሻው ወያኔ አንግቦት የተነሳበት ዓላማው የተሳሳተ፣ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህም የተሳሳተ ዓላማ በተለያዩ ወቅቶች…

ሙሉ ለሙሉ በዓድዋ ተወላጆች ቁጥጥር ስር የዋለው የቀድሞው የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) እና የአሁኑ የዓድዋ ነፃ አውጭ ግንባር የማዕከላዊ ስራ አስፈጻሚ አባላት ስም ዝርዝር ስዩም ተሾመ ይህን በሚመለከት የጻፈው በመጀመሪያ ከሩቅ ሲያዩት #ብሔርተኛ ይመስላል። ትንሽ ጠጋ ስትለው #ጎሰኛ ይሆናል።…