የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ወደ ሃዋሳና አዲስ አበባ እየሄዱ ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010)  በደቡብ ክልል ጌዲዮ ዞን የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች አካባቢውን እየለቀቁ ወደ ሃዋሳና አዲስ አበባ እየሄዱ መሆናቸው ተነገረ። በአካባቢው ሃብትና ንብረት አፍርተው ይኖሩ የነበሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ስፍራውን ለመልቀቅ የተገደዱት በጌዲዮ ተወላጅ አመራሮች ጫና እየደረገባቸው በመሆኑ ነው ሲሉ የኢሳት…

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) በወልዲያ ትላንት የተጀመረው የህዝብ ተቃውሞ ወደ ሌሎች አካባቢዎች መዛመቱን ተከትሎ የህወሃት መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር በየከተሞቹ ማስገባቱ ተገለጸ። በወልዲያ፣ ሀይቅ፣ ቆቦ መውጪያና መግቢያ ላይ በርካታ ወታደሮች የሚገኙ ሲሆን የሚወጣና የሚገባ ተሽከርካሪ እያስቆሙ እንደሚፈትሹ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።…
አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት የለም አሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) የሕወሃት ስራ አስፈጻሚ በመሆን በቅርቡ የተመረጡት የቀድሞው የኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር የለም ሲሉ አስተባበሉ። አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ የበላይነት አለ ማለት ልጆችን አያ ጅቦ መጣብህ እያሉ እንደማስፈራራት ይቆጠራልም ብለዋል። የአማራና…
የሱዳን ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገቡ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) የሱዳን ወታደሮች 40 ኪሎ ሜትር ያህል ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ ክልል በመግባት ሰብል ማቃጠላቸውን የኢሳት ምንጮች አጋለጡ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ወታደሮቹ በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ኮርመር እስከሚባል አካባቢ ዘልቀው መግባታቸው ታውቋል። አሰሪ የተባለውን የኢትዮጵያ መሬት መቆጣጠራቸውንም…
ዜግነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ጎብኚ ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 25/2010) በኢትዮጵያ አፋር ክልል ማንነታቸውና ዜግነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ጎብኚ ተገደሉ። ጎብኚውን ሲያዘዋውር የነበርው ሹፌርም መገደሉ ታውቋል። የኢሳት ምንጮች ከስፍራው እንደገለጹት ዛሬ በአፋር ክልል ኤርታሌ በተባለው ወረዳ የተገደሉት ጎብኚ ወደ ኤርታሌ እሳተ ጎመራ በመጓዝ ላይ ነበሩ። ወደ አካባቢው ሰርገው…