በኢራን እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ በኢራን ጠላቶች የተቆሰቆሰ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በኢራን እየተካሄደ ያለውን ጸረ መንግስት ተቃውሞ የሀገሪቱ መንፈሳዊ መሪ በኢራን ጠላቶች የተቆሰቆሰ ነው ሲሉ ወነጀሉ። መንፈሳዊ መሪው አያቶላ አሊ ካሚኒ ባለፈው ሐሙስ ተቃውሞ ከተነሳ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ንግግር ጠላቶች ያሏቸውን አካላት በግልጽ አልተናገሩም። በኢራን እየተካሄደ ባለው…
ተከሳሾች ዳኞችን በችሎት ላይ መናገራቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በግንቦት 7 ስም በሽብር ወንጀል ተከሰው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተከሳሾች ከሳሞራና አባይ ጸሃዬ በላይ ተጠያቂ ናችሁ ሲሉ ዳኞቹን በችሎት ላይ መናገራቸው ታወቀ። ፍርድ ቤቱም በተከሳሾቹ ላይ እስከ 16 አመታት የሚዘልቅ እስራት የወሰነ ሲሆን…
ከተድባበ ማርያም ገዳም ጽላት ተሰረቀ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በአማራ ሳይንት ከሚገኘው ተድባበ ማርያም ገዳም ጽላት መሰረቁን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በዚህም የአካባቢው ምዕመናን የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ መሆናቸው ታውቋል። በሌላም በኩል በምዕመናን ተቃውሞ ሲቀርብባቸው የቆየው የአዲስ አበባው ሳህሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደብደበው ሆስፒታል መግባታቸው…
ባሻምቡ ወለጋ ተቃውሞ ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል በመንግስት ላይ የተጀመረው ተቃውሞ አሁንም መቀጠሉ ተገለጸ። ዛሬ ባሻምቡ ወለጋ በኦሮምኛና በአማርኛ የተጻፉ መፈክሮችን ይዘው አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ አንድ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የኦሮሚያ ክልል…
ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ። በኢንጪኒ አደአበርጋ ህዝብ አደባባይ በመውጣት የህወሀትን ስርዓት አውግዟል። በአዳማ ዩኒቨርስቲ 18 ተማሪዎች ተባረዋል። የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል። በምስራቅ ወለጋ በገሊላ የአጋዚ ወታደሮችና ህዝቡ ፍጥጫ ውስጥ…