ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የሞ ኢብራሔም ፋውንዴሽንን ሽልማት አሸነፉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የሞኢብራሔም ፋውንዴሽንን የ5 ሚሊየን ዶላር የመሪነት ሽልማት አሸነፉ። በአለም ላይ ከፍተኛ የሆነውንና ከኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች የበለጠ የገንዘብ ስጦታ የሚያስገኘውን የአፍሪካ የመሪነት ሽልማት ከሞኢብራሒም ፋውንዴሽን በማግኘት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ 5ኛ ሆነዋል። ሰርሊፍ…
የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እስከ 16 አመታት የሚደርስ የእስር ቅጣት ተወሰነባቸው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) አራት የመከላከያ አባላትን በመግደል አስር አቁስለዋል የተባሉ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እስከ 16 አመታት የሚደርስ የእስር ቅጣት ተወሰነባቸው። ድርጊቱን የፈጸምነው ለትልቅ ሃገራዊ አላማ እንጂ ለግል ጥቅማችን አይደለም ሲሉም ተከሳሾቹ በችሎት ውስጥ መናገራቸው ተመልክቷል። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት…
የኦፌኮ አመራሮች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወሰነ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 7 የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ አመራሮች ክሳቸው እንዲቋረጥ መወሰኑን የፌደራል አቃቢ ሕግ አስታወቀ። በዚሁም መሰረት አቶ በቀለ ገርባ፣ጉርሜሳ አያና፣አዲሱ ቡላላ፣ደጀኔ ጣፋ፣ጌቱ ጋሩማ፣ተስፋዬ ሊበንና በየነ ሩዳ ክሳቸው ተቋርጧል። የእነ አቶ በቀለ ገርባ ክስ በዚህ…
የአገዛዙ ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ ከ4 በላይ ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) በሐረር ከተማ በሃማሬሳ የስደተኞች ጣቢያ በሰፈሩ ሰዎች ላይ የአገዛዙ ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ ከ4 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። በጥቃቱ በአጋዚ ታጣቂዎች ከተገደሉት መካከል አንድ የኦሮሚያ የጸጥታ ፖሊስ እንደሚገኝበትም ታውቋል። ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች እስከ 1 ሚሊየን እንደሚጠጉ…
በአገዛዙ የፖሊስና የሚሊሺያ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 5/2010) በጎንደር ጯሂት በአገዛዙ የፖሊስና የሚሊሺያ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ መወሰዱ ተገለጸ።10 የአገዛዙ ሃይሎች መገደላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ካለው የስራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። ከባህርዳር ወደ…
በኦሮሚያ ለሶስት ቀናት የተጠራው አድማ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) በኦሮሚያ ክልል ለሶስት ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ተጀመረ። በአብዛኞቹ የክልሉ ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች አድማው በተሳካ ሁኔታ በመካሄድ ላይ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች አድማው ተጠናክሮ ሲካሄድ ከአዲስ አበባ የሚወጡ…
ክብር ስለሚጨፈጨፈው ወገናቸው ለሚቆረቆሩ የአማራ ካህናት!

 (ከታዘቢ) የወያኔ ስርአት የአማራ ነው በማለት በአማራ አምሳል አንቋሾ በማቅረብ ለማጥፋት ብዙ ከደከመባቸው መካከል ካህናት ግንባር ቀደም ናቸው። ጥቂት ከስርአቱ ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸውንና ወንጀልን ከአለማዊ ሰው በበለጠ የሚፈፅሙ ካህናትን ወደ ቤተክርስቲያን በማስገባት አማራ ካህናትን ከስራ መደባቸው አፈናቅሎ ነገር ግን…

(ምስጋናው አንዱዓለም) በዚህ ወቅት የአድዋ ድልና መሪው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ መታሰቢያነት ስለ ትግራይ ብሄረተኝነት፣ ስለኢትዮጵያ ብሄረተኝነት፣ ስለ ጉራጌ ብሄረተኝነት እና አማራ ብሄረተኝነት ትንሽ ማለት አስፈላጊ ነው፡፡ እንደሚታየው የትግራይ ብሄረተኝነት ቁንጮ የሆነው ህወሀት የኢትዮጵያን ብሄረተኝነት ለ42 አመታት ሲዋጋና ሲያደማ…

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ) ይህ ታሪካው ሰነድ አስደግፌ ብዙ ሰው ያላወቀውን ሰነድ/ጽሑፍ ስታዩ የቬሮኒካን ጽሑፍ የለጠፋችሁ እኔ ያላየሁዋችሁ ድረገጾች ካላችሁ እባካችሁ ይህንን የኔን መልስ ኮፒ/በማድረግ ድረገጾቻችሁ ላይ ለጥፉት። በስንት ድካምና ምርምር ያገኘሁት ሰነድ ስለሆነ፤ ሙያችሁም ለማስተማር ከሆነ በአድልዎ ሃይቅ…