በአፍጋኒስታን በተፈጸመ ጥቃት 29 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010) በአፍጋኒስታን ርዕሰ መዲና ካቡል አሸባሪዎች ባደረሱት ጥቃት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 29 ሰዎች ተገደሉ። የአፍጋኒስታን የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት እንደገለጹት ከሁለት ተከታታይ ፍንዳታዎች በኋላ ከሞቱት 29 ሰዎች በተጨማሪ 49 ሰዎች ቆስለዋል። አለም አቀፉ የአሸባሪ ቡድን አይሲስ በጥቃቱ ሃላፊነትን ወስዷል። ዛሬ…
የገዛህኝ ነብሮ የቀብር ስነስርአት ብዙዎችን ያስደነቀ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010) በደቡብ አፍሪካ ከሃገሪቱ ዜጋ ውጪ ባልተለመደና በደመቀ መልኩ የተከናወነው የገዛህኝ ነብሮ የቀብር ስነስርአት በዙዎችን ያስደነቀ ሆኖ ማለፉ ተገለጸ። የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቴሌቪዥንም ለቀብር ስነስርዓቱ የዜና ሽፋን በመስጠት ኢትዮጵያውያን የማህበረሰብ መሪያቸውን በታላቅ ሀዘን ሸኙት ሲል በዘገባው አስደምጧል። የአክቲቪስት…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010)የሶማሌ ክልል የፍትህ ጥምረት የተሰኘ የፖለቲካ ንቅናቄ በይፋ ተመሰረተ። ጥምረቱ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የምስረታ ጉባዔውን አካሂዷል። በሶማሌ ክልል እየተፈጸመ ያለውን መጠነ ሰፊ ጭቆና ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር በመሆን ይታገላል ይላል በይፋ የወጣው የጥምረቱ ጋዜጣዊ መግለጫ። ፋይል የተበታተነውን የሶማሌ…
ከካማሽ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች  እየተንገላቱ ናቸው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010) ከቤንሻንጉል ጉምዝ አካባቢ ካማሽ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች  በባህርዳር ቴክኒክና ሙያ ቅጥር ግቢ ሰፍረው እየተንገላቱ መሆናቸው ተነገረ። ሃብት ንብረታቸው ወድሞባቸው ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉት 120 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ከሰው ጋር እንዳይገናኙ ተደርገው እየተጎሳቆሉ ይገኛሉ ተብሏል። የብአዴን አመራሮች ጉዳዩን…

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ22/2010) ሜድሮክ የወርቅ ማዕድን በሻኪሶ ስራውን እንዲቀጥል መወሰኑን ተከትሎ በአካባቢው ሕዝብ ዘንድ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። በጉጂ ዞን ሻኪሶና ፊንጫ ከተማ ከጠዋት ጀምሮ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። ሜድሮክ ኢትዮጵያ የወርቅ ማእድን የማውጣት ስራውን እንዲያቆም ከተደረገ ከ1 ዓመት በኋላ በድጋሚ ፈቃድ…
የኢሳት 8ኛ አመት በአል በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2010) በመላው አለም በሚገኙ 50 ከተሞች የተዘጋጀው የኢሳት 8ኛ አመት በአል በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ። በአሜሪካ፣አውሮፓ፣በውስትራሊያ እንዲሁም በሩቅ ምስራቅና በመካከለኛው ምስራቅ በአንድ ቀን የተዘጋጀው የኢሳት 8ኛ አመት ክብረ በአል በርካታ እንግዶች በታደሙበት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁም ተመልክቷል። የኢሳት ሶስት ስቱዲዮዎች…

ዜና አቢሰሎም ፍሰሃ በነጻነት ታጋዩ በገዛኽኝ ነበሮ ህልፈተ ህይወት ምክንያት ከመላዉ አለም የተሰባሰብቡት የቀድሞ የመከላከያና የፖሊስ ባልደረባዎች በመስራች ጉባኤዉ ላይ ተገኝተዋል። ስብሰባዉን በመክፈቻ ንግግር የመሩት ሻለቃ ደምሴ ዮሐናስ በሀምሳ አለቃ ገዛኝ ነብሮ የክብር ሞት ምክንያት የተሰማቸውን ዉስጣዊ ስሜት ከገለጹ በኍላ…

በሞያሌ አሁንም የፀጥታ ሁኔታ ባለመሻሻሉ እየተቸገሩ መሆናቸዉን ነዋሪዎች ተናገሩ። ሰሞኑን በከተማዋ በነዋሪዎች ላይ የእጅ ቦምብ ሊወረዉሩ የነበሩ ሰዎች ላይ ቦምቡ ፈንድቶ በራሳቸዉ ላይ ጉዳት እንዳደረሱ በአካባቢዉ የነበሩ የዐይን ምሥክሮች ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።

በምስራቅና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲቀርብበት የነበረው የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ተጨማሪ የ10 አመት የኮንትራት ስምምነት ማግኘቱን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ስምምነቱን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በአዶላ ወዮ…

በሽንሌ ዞን እስርና ድብደባው እንደቀጠለ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮ-ሶማሊ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የክልሉ የልዩ ሃይል አባላት በርካታ ወጣቶችን እየያዙ አስረዋል። ብዙዎችም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ብዙዎቹ ወደ ጅግጅጋ ተወስደው የታሰሩ ሲሆን፣ በእስር ቤት ውስጥም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።…

ኢንሳ አሁንም ትርምስ ላይ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢንሳን ለረጅም ጊዜ ሲመሩ የነበሩት ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/አረጋዊ ከለቀቁ በሁዋላ ስልጣናቸውን በሚለቁ የህወሃት ባለስልጣናት ቦታ ሌሎች አዳዲስ ሰዎች እየተተኩ ነው። የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ…