የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ጥለው ወጡ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 4/2010) የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተቋሙ ውስጥ ምግብ በመከልከላቸው ግቢያቸውን ጥለው መውጣታቸው ተነገረ። ተማሪዎቹ በዩኒቨርስቲው የሚቀርብላቸው ምግብ በመቆሙ ሕይወታቸውን ለማቆየት ግቢያቸውን ለቀው ወደ ሐሮማያ ከተማ ለመሔድ ተገደዋል። ዩኒቨርስቲው ለተማሪዎቹ ምግብ እንዳይሰጥ የከለከለው በግቢው ውስጥ የትምህርት ማቆም አድማ በመጀመሩ ነው…

በሶማልያ የታችኛው ሸበሌ ክፍለ ሃገር በባራዌ ከተማ ዛሬ በኳስ ጨዋታ ሥፍራ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ በትንሹ አራት ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ የፀጥታ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ሌሎች አሥራ ሦስት መቁሰላቸውም ተነግሯል።

የኢህአዴግ ነባር አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የኢህአዴግን መስመር ያስቀጥላል የሚል እምነት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 04 ቀን 2010 ዓ/ም) ነባሮቹ የኢህአዴግ አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢህአዴግን መስመር የማስቀጠል ፍላጎት አለው ብለው እንደማያምኑ እየተናገሩ ነው። የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት…

የወልቃይት ተወላጆች አዲስ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 04 ቀን 2010 ዓ/ም) የአዲ ረመጥ ወረዳ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንዳመለከቱት “የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ትግራይ ቅርንጫፍ” የካቲት 2 ቀን 2010 ዓም አዲስ ክስ…

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሦሪያ ተፈጸመ የተባለውን ኬሚካዊ የጦር መሣሪያ ጥቃት አስመልክቶ በዛሬው የትዊተር መልዕክታቸው “ዩናይትድ ስቴትስ በሦሪያ ላይ ጥቃት የምትከፍትበትን ቀን ፈፅሞ አልተናገርኩም” ብለዋል። “ጥቃቱ ፈጥኖም፣ ዘግይቶም ሊካሄድ ይችላል” ይላል የትዊተር መልዕክታቸው።

“የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ በአሜሪካ ምክር ያለፈውን ሕግ ይቀበል የሚሉ የዋሆች አሉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካን ሕግ መቀበል የለበትም” ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “የአዲሱ ጠ/ሚንስቴራችን የመጀመሪያ ስራቸው መሆን ያለበት የሶሻል ሚድያ አጠቃቀማችን ላይ ህግ ማውጣት ነው” ኃይሌ ገብረስላሴ — ፕሮፌሰር መስፍን ሰሞኑን…

(አያሌ መንበር) ክፍል ስድስት ከክፍል 1 – 4 ያለውን ከዚህ ላይ  እንዲሁም ክፍል 5 ከዚህ ላይ ያንብቡ የወልቃይትን የአማራ ማንነት ጥያቄ በተመለከተ ምናልባት እንገደና አሁን መለስ ብሎ ገምግሞ ችግሩን ተመልክቶት ካልሆነ በስተቀር የብአዴን አቋም ግልጽ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ወልቃይትን…

የትግሬ ወያኔ መንግስት አዲስ ክስ ከመሰረተባቸው የወልቃይት አማራ ብሄርተኝነት የኮሚቴ አባላት መካከል 1ኛ. አቶ አባይ ማሞ 2ኛ. አቶ ክብርአብ ስማቸው 3ኛ. አቶ ታምራት ደሳለኝ 4ኛ. መምህር ፈረደ በሪሁን 5ኛ. መምህር እንዳለው ብርሃኔ 6ኛ. መምህር ልዑል ሐጎስ 7ኛ. መምህር ሞላ አበላይ 8ኛ.…