ሰበር ዜና – ጉዳያችን (ኦድዮ) በሀገር ቤት እና በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል አዲስ ንግግር ሊጀመር ነው ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com
በሐዋይ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010)  በሐዋይ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ተቀሰቀሰ። የኪላዊያ እሳተ ጎሞራ ፍንዳታን ተከትሎም 2 ሺ የሚጠጉ ሰዎች በአስቸኳይ ከቀያቸው እንዲነሱ ተደርገዋል። ትልቅ ስፋት አለው በተባለው ደሴት የተከሰተው እሳተ ጎመራ ፍንጣቂ ወደ ዛፎችና መንገዶች ላይ መወርወር መጀመሩ ደግሞ አደጋውን የከፋ አድርጎታል…
በባህርዳር ስታዲየም ሊካሄዱ የነበሩ ጨዋታዎች ተሰረዙ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) የጸጥታ ስጋት በሚል ሰበብ በባህርዳር ስታዲየም ሊካሄዱ የነበሩ ጨዋታዎች ተሰረዙ፡፡ ፋይል ሚያዝያ 26 /2010 ባህርዳር ከነማ ከኮምቦልቻ ከነማ እንዲሁም አውሥኮድ እግር ኳስ ክለብ ከሰበታ ከነማ ክለብ ጋር ዛሬ የነበረው ጨዋታ ተሰርዟል። ውድድሩን ለመመልከት ሜዳ የገቡ ተመልካቾች ጨዋታው…
የባህርዳር ሁለገብ ስታዲየም ሳይጠናቀቅ ርክክብ ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) በባህርዳር የተገነባው ሁለገብ ስታዲየም ሳይጠናቀቅ የአማራ ክልል መንግስት ከሜድሮክ ኢትዮጵያ ጋር የርክክብ ስነስርአት ፈጸመ። ፋይል በ7 መቶ ሚሊየን ብር ተገንብቶ በ5 አመት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው የባህርዳር ሁለገብ ስታዲየም የጣራና የወንበር ተከላ ሳይጠናቀቅ የአማራ ክልላዊ መንግስት ርክክብ ፈጽሟል።…
በሕወሃትና በዋልድባ መነኮሳቱ መካከል ያለው ውዝግብ 40 አመታትን አስቆጥሯል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) በቅርቡ ከወህኒ የተለቀቁት የዋልድባ መነኮሳት በሕወሃትና በመነኮሳቱ መካከል ያለው ውዝግብ 40 አመታትን ያስቆጠረ መሆኑን ይፋ አደረጉ። ሕወሃት ጫካ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ በገዳሙ ሰላዮቹን ማሰማራቱን ይናገራሉ። መነኮሳቱ አባ ገብረኢየሱስና አባ ገብረስላሴ በገዳሙ መጸለይ ወንጀል ሆኖ በመከላከያ ሰራዊቱ መደብደባቸውን…
በድሬዳዋ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) በድሬዳዋ የሶማሌ ክልሉን ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌን በመቃወም ሰልፍ ተደረገ። ዛሬ ከጁማአ ስግደት በኋላ በተደረገው ተቃውሞ የአብዲ ዒሌ አስተዳደር ከስልጣን እንዲወርድ ተጠይቋል። የሶማሌ ክልልን በሰፊው ያዳረሰው ተቃውሞ በቀጠለበት በዚህን ወቅት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ሃላፊ…
የገዛህኝ ነብሮ ግድያ ሆን ተብሎ የታቀደ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) የኢትዮጵያውያን የመብት ተሟጋች ገዛህኝ ገብረመስቀል ነብሮ ግድያ ሆን ተብሎ የታቀደ መሆኑን አንድ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ገለጸ። ሳምንታዊው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ ሜይል ኤንድ ዘጋርዲያን በዛሬው እትሙ ግድያው ከዘረፋ ጋር ያልተያያዘ መሆኑን የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።…
በደቡብ አፍሪካ ሰባት ኢትዮጵያውያን ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 26/2010) በደቡብ አፍሪካ በ48 ሰዓታት ውስጥ ሰባት ኢትዮጵያውያን መገደላቸው ተሰማ። ከጆሀንስበርግ በ60 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ፓልም ሪች ወይም ቶኮዛ በሚባል አካባቢ ከትላንት ወዲያ ጀምሮ እስከዛሬ ጠዋት ድረስ 7 ኢትዮጵያውያን የተገደሉት በተደራጁ ዘራፊዎች በተወሰደ ርምጃ መሆኑ ታውቋል። 5ቱ የተገደሉት…

በድሬዳዋ ከጁምዓ ሰላት በሁዋላ የአቶ አብዲ ኢሌን አገዛዝ በመቃወም ህዝቡ ሰልፍ አደረገ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 26 ቀን 2010 ዓ/ም)ላለፉት ሳምንታት በሽንሌ ዞን የአብዲ ኢሌ አገዛዝ በህዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ፣ አፈናና እስር በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም በድሬዳዋ ከተማ በተለያዩ መስኪዶች…

በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ስም ከተዘጋጀው ተዘዋዋሪ ብድር ከሶስት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ መባከኑ ተጋለጠ፡፡ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 26 ቀን 2010 ዓ/ም)በአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት 312 ሚሊዮን 641 ሽህ ብር በላይ ማባከኑን የክልሉ ኦዲት ሪፖርት…

በባህርዳር ፖሊሶች አንዷን እስረኛ ከእስር ቤት አውጥተው ደፈሯት (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 26 ቀን 2010 ዓ/ም) በባህር ዳር ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ እመቤት አዳነ የተባለች በጥርጣሬ የታሰረችን እስረኛ የምሽት ተረኛ ጠባቂዎች ከእስር ቤት በማውጣት አስገድደው ደፍረዋታል። እስረኛዋ ለጣቢያው የምርመራ ክፍል ሃላፊ…

በጅቡቲ ወደብ የሚገኙት የቻይናና አሜሪካ ሰራዊት እየተወዛገቡ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 26 ቀን 2010 ዓ/ም) በጅቡቲ ሊሞኒየር ወደብ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ጄቶች ከቻይና የጦር ሰፈር በሚለቀቁ ጨረሮች እየተጠቁ መሆኑን አሜሪካ ስታስታውቅ ቻይና በበኩሏ ክሱ መሰረተ ቢስ ነው ብላለች። ፋይናንሻል ታይምስ…