ፖለቲካ “ጥቅምን አስልቶ የሚደረግ ጨዋታ” ነው። ጥቅሙ ለግል ወይም ለብዙሃኑ ሊሆነ ይችላል። በዚህ መነጽር ካየነው የኦዴግ አገር ቤት መግባትም አስገራሚ ዜና ሊሆን አይችልም።
በእስራኤል ጋዛ ድንበር በተነሳ ተቃውሞ 37 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) አሜሪካ ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ማዛወሯን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ 37 የሚሆኑ ፍልስጤማውያን ተገደሉ። በጋዛ ድንበር የእስራኤል ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ከ1 ሺ 3 መቶ በላይ ፍልስጤማውያን መቁሰላቸውም ታውቋል። አሜሪካ ዛሬ ቢሮዋን በይፋ ከቴላቪቭ ወደ ወደ ኢየሩሳሌም ማዛወሯን ተከትሎ በሚደረገው…
ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በዘመናዊ የወላይትኛ ሙዚቃው ከፍተኛ  ዕውቅናን ያገኘው ኮይሻ ሴታ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ማረፉን ለማወቅ ተችሏል። የወላይትኛን ሙዚቃ በዘመናዊ መልክ በመጫወት ፈር ቀዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ 2 አልበሞችን ለአድማጮቹ…

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) በአሜሪካን የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን የጠሩት ስብሰባ በተቃውሞ መበተኑ ተገለጸ። ባለፈው ቅዳሜ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ብሉሚንግተን ከተማ የተጠራውን ስብሰባ በአካባቢው የሚኖሩ የተለያዩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲዎች ባሰሙት ተቃውሞ ተቋርጧል። በተለይም የሶማሌ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጥር ወደ ስብሰባ አዳራሽ በመግባት እንዲቋረጥ…

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት መባባሱ ተገለጸ። ፋይል በጤፍ፣ በበርበሬ፣ በዘይት፣ በስኳር፣በቲማቲምና በተለያዩ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ኢሳት ወደ ተለያዩ ከተሞች በመደወል ካሰባሰበው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። በተለይም በከተሞች እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ህዝቡን እያማረረው መሆኑም ታውቋል። መንግስት…
ኦዴግ ከሕወሃት መንግስት ጋር የተናጠል ድርድር ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010) የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/ከመንግስት ጋር የተናጠል ድርድር ጀመረ። ቀጣዩን ድርድር በአዲስ አበባ ለማካሄድ የኦዴግ መሪዎች ሰሞኑን አዲስ አበባ እንደሚገቡም ተገልጿል። በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/ድርድሩን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ከመንግስት ከተላኩ ሁለት ልኡካን ጋር መወያየቱን ገልጿል።…

በቀብሪ ደሃር እስር ቤት ውስጥ በስቅላት የተገደለችውን የ24 አመቷ ወጣት ሞት ለማስተባበል እየተሞከረ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ/ም) ዘመዶችሽ እኔን ሊከሱ ወደ አዲስ አበባ ሄደዋል በሚል ምክንያት በኢትዮ-ሶማሊ ክልል መሪ በአቶ አብዲ ኢሌ ወታደሮች በቀብሪ ደሃር እስር…

በአርበኞች ግንቦት7 የተከሰሱት በፍርድ ቤት ውስጥ መፈክር አሰሙ (ኢሳት ዜና ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ/ም) በእነ ሚፍታህ ሸህ ሱሩር ክስ መዝገብ በአርበኞች ግንቦት 7 ተከሰው ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡ በቁጥር ከ40 በላይ የሚሆኑ ተከሳሾች በፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ መፈክር አሰምተዋል።…

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2010)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ከአቡነ ማትያስ ጋር በእርቅ ጉዳይ ላይ መነጋገርቸውን አስታወቁ። በውጭ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ሰላም በሚወርድበት ሁኔታ ላይ ከፓትሪያርኩ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል። ዶክተር አብይ አሕመድ የደርግ…

ሃዋሳ በከፍተኛ የውሃ ችግር ተጠቅታለች ተባለ (ኢሳት ዜና ግንቦት 06 ቀን 2010 ዓ/ም) የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት የአዋሳ ህዝብ ንጹህ ውሃ ያገኛል ብሎ መናገር የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። በ15 ቀናት ውስጥ ለአንድ ወይም ለ2 ቀናት ለተወሰኑ ሰዓታት ውሃ ካገኙ በሁዋላ መልሶ…

ለበርካታ ጋዜጠኞች ከሥራ መፈናቀል፤ ከአገር መሰደድ ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅነት የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ የነበረው ዘርዓይ አስገዶም ከሥልጣኑ ተነስቷል። አንደበቱ በቅጡ ያልተገራና ፍጹም የህወሓትን ዓላማ በአደባባይ በማስፈጸም የሚታወቀው ዘርዓይ፤ ከዚህ እንደፈለገ ከሚነዳው መ/ቤት መልቀቁ በሚዲያው ማኅበረሰብ ዘንድ…