የዳንጎቴ ሲሚንቶ ሰራ አሰኪያጅና ሁለት የስራ ባልደረቦቻቸው ተገደሉ

የፋብሪካው ስራ አስኪያጂ የነበሩት ዲፕ ካማራምንጭ :ኢትዮጵያን ሪፖርተር ቦርከና ግንቦት 8 2010 ዓ ም በኦሮሚያ ክልል ኢንጪኒ ወረዳ የዳንጎቴን ሲሚንቶ ፋብሪካን በዋና ስራ አስካሂጅነት የሚመሩት ዲፕ ካማራ ሹፌራቸውና እንዲሁም የ ሶሰት ልጆች እናት የሆነችው ጸሃፊያችው ባልታወቁ ታጣቂዎች እንደተገደሉ ታውቌል ፤…

በቅዱስ ራማዳን ወር የሚከናወነው የፆም ሥርዓት አላህን ለመፍራት እንደሚያግዝ አዲስ አበባ የሚገኙ የእሥልምና መምህር በቪኦኤ ባስተላለፉት መልዕክት ተናግረዋል።

የኦሕዴድና የብአዴን ልዩነት ( አቻምየለህ ታምሩ ) 1. ኦሕዴድ ለተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች ጊዜያዊ መጠለያ ከመስራት ጀምሮ የተፈናቃዮችን ደህንነት በተቻለ መጠን ለመጠበቅ ሲሞክር፤ ነውረኛው ብአዴን ግን ለተፈናቃዮቹ ጊዜያዊ መጠለያ መስራት ይቅርና ያስጠለላቸው ቤተ ክርስቲያን እንኳ ማረፊያ እንዲነሳቸውና ከግቢው እንዲያስወጣቸው ትዕዛዝ በማስተላለፍ…

“አቦይ ስብሃት” በሚል መጠሪያ የሚታወቁትን አንጋፋውን የሕውሓት መሥራች አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በጡረታ እንዲያርፉ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት አስታወቋል፡፡
የተክሌ አቋቋም ሊቁ መምህር እንደሥራቸው ከተሰወሩ እነኾ 24 ዓመት ኾነ፤ ዳግማዊ አለቃ ተክሌን መልሱልን

አሁን ያሉን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ መምህር እንደሥራቸው በታሰሩበት ቦታ በቅርቡ አንድ ልኡክ ጉብኝት አድርጎ ነበር፡፡ መምህር እንደ ሥራቸው፣ መመንኮሳቸውንና አዘውትረው የሚጸልዩትም በአንድ እግራቸው ቆመው መኾኑን አመልክተዋል፡፡ አሁን ዕድሜያቸው ወደ 74 ዓመት የተጠጋውን እኒህን አረጋዊ የተክሌ ምትክ እባካችሁ ፍቱልን፡፡~~~~~~ /ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን…

ከ100 ሺ በላይ የሚቆጠሩ የጌዲዮ ተወላጆች ከጉጂ ዞን ተፈናቅለው ገደብ ከተማ ገቡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሳምንታት በፊት በጉጂ ብሄረሰብ አባላትና በጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት መካከል ተነስቶ የነበረው ግጭት ተከትሎ ከ200 ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው የነበረ ቢሆንም፣ ግጭቱን…

የአፋር ወጣቶች የጅቡቲን መስመር ዘግተው አመሹ (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ወጣቶቹ እርምጃውን የወሰዱት ከህዳር 26 ጀምሮ በደህንነት አባላት ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ እስከዛሬ ድረስ ያለበት ያልታወቀው የሰመራ ዩኒቨርስቲ የሰው ሃይል አስተዳደር ሃላፊ አቶ ሳሊህ ረሺድ እንዲፈታ ለመጠየቅ ነው።…

የመቱ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አድማ በማድረግ ላይ ናቸው (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ተማሪዎቹ አድማውን የጀመሩት ከጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ተፈናቅለው በመቱ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተደረጉት ተማሪዎች ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ መወሰኑን ተከትሎ ነው። ተማሪዎቹ አስተማማኝ ሰላም በሌለበትና ለህይወታችን…

አለማቀፍ የኡንዲስትሪያል ህብረት የኢትዮጵያ ሰራተኞች የተሻለ ክፍያ እንዲያገኙ ዘመቻ ጀመረ (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ውስጥ በጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዱስትሪዎች የሚሰሩ ሰራተኞች የተሻለ ክፍያ እንዲያገኙ ለማድረግ ኢንዳስትራያል ግሎባል ዩኒየን የተባለው የሰራተኞች ማህበር ዘመቻ ጀምሯል። በእነዚህ እንዱስትሪዎች ውስጥ ተቀጥረው…

ትላንት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አበጥር ወርቁ በተባለ የአማራ ብሔር ተወላጅ ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግፍ ተመልክተናል፡፡ ይህ ከመሆኑ ከአንድ በፊት ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ527 በላይ አባወራዎች በድምሩ 2000 ከሚሆኑ ቤተሰቦቻቸው ተፈናቅለዋል፡፡ እነዚህ “ሕገ ወጥ ናችሁ” በሚል ሰበብ ተዘርፈውና ተደብድበው የተፈባቀሉት…